Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 22 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾመ።

ወይዘሮ ኬሪያ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ ለምክር ቤቱ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተከትሎ ነው።

ምክር ቤቱም ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የቀድሞውን አፈ ጉባኤ የስራ መልቀቂያ ተቀብሎታል።

ሹመቱም በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

ወይዘሮ ኬሪያ የትግራይ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።