Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በትግራይ ያለውን ድህነት በመቅረፉ ረገድ ምሁራን የበኩላቸውን ሊያበረክቱ ይገባል- ዶ/ር ደብረፅዮን


አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል ድህነትን በመቅረፉ ረገድ ምሁራን የበኩላቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለፁ።

ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት ዛሬ በመቐለ ከተማ ምሁራንን ያሳተፈ መድረክ ሲጀመር ነው።

የመድረኩ አላማም ምሁራኑ ከመንግስት ጋር በመቀራረብ ድህነትን ለመቅረፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

በዚህም በመድረኩ ከ10 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን፥ ጥናታዊ ፅሁፎቹ የህዝብ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ ሃሳቦች በማምጣት የላቀ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ነው የተባለው።

በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ዶክተር ደብረፅዮን፥ መድረኩ መንግስትና ህወሓት ባካሄዱት ጥልቅ ተሃድሶ ለተለዩ ችግሮች የበኩሉን መፍትሄ የሚያቀርብ መሆመኑን ተናግረዋል።

ስለሆነም መንግስት ድህነት በመቀነስ እየሰራ እንዳለለ የገለፁ ሲሆን፥ ይህም በጥናት እና ምርምር የተደገፈ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ መድረክ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም መንግስት እያደረገ ላለው ጥረት በተግባር በመደገፍ ምሁራኑ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የመድረኩ ተሳታፊ ምሁራን በበኩላቸው፥ በመድረኩ የቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፎች በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩሩ እና ድህነትን ለመቀነስ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ገልፀዋል።

መድረኩ ምሁራኑ ከመንግስት ጋር ተቀራርበው ለመስራት መዘጋጀታቸውን የሚያሳይ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዛሬ የተጀመረው ምሁራን የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ የፌዴራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራን እየተሳተፉበት ይገኛል።

በዮናታን ግዛቸው