አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፊታችን አርብ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው።
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች ለአንድ ወር በእረፍት ላይ የሚገኙ የምክር ቤቱ አባላት ለአስቸኳይ ስብሰባው እንደተጠሩ አረጋግጠዋል።
የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 58 ንኡስ አንቀፅ 4 እንደተደነገገው፤ ምክር ቤቱ እረፍት ላይ በሚሆንበት ጊዜ አፈ ጉባዔው ስብሰባ ሊጠራ ይችላል።
እንዲሁም የምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብም በአንቀጽ 15 “ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል” ይላል።
በዚህም መሰረት የምክር ቤቱ አፈጉባዔ ለፊታችን አርብ የካቲት 23 2010 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።
አባላቱም ከነገ ጀምሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዋል።