Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ሰበር ዜና: የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ


አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን አመራር ምደባ ማስተካከያ አደረገ።

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት፣ ተሳትፎ ለማጠናከር እና በክልል እና ሀገር ደረጃ የተጀመሩ ማሻሻያዎችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም ኦህዴድ እና የክልሉ ህዝብ የጀመረው ትግል አሁን ከደረሰበት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሲባል የአመራር ምደባ ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ዶክተር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር እና አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

የአመራር ምደባ ማስተካከያውም በኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መፅደቁን ድርጅቱ አስታውቋል።

በዛሬው እለት የተመረጡት አመራሮችም የክልሉን እና የሀገሪቱን ህዝቦች ጥቅም የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ታምኖባቸዋል ብሏል ድርጅቱ።

በመሆኑም የኦህዴድ አባላት፣ ደጋፊዎች፣ የክልሉ እና መላው የሀገሪቱ ህዝብ ከኦህዴድ ውሳኔ ጎን በመሰለፍ በሀገር ደረጃ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመዘገብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከድርጅቱ ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል።