Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በባለፈው ስብሰባው ባልቋጫቸው ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ነው


አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ማዕከላዊ ኮሚቴ በባለፈው ስብሰባው ባልቋጫቸው ጉዳዮች ላይ ዛሬ በመቀሌ ከተማ መወያየት ጀመረ።

ማእከላዊ ኮሚቴው ማዕከላዊ ኮሚቴው ከመስከረም 22 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን በመቀሌ ከተማ ስብሰባ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

በዛሬው እለትም በባለፈው ስብሰባው ባልቋጫቸው ጉዳዮች ላይ እየመከረ መሆኑ ነው የተነገረው።

ዛሬ በተጀመረው ስብሰባ በ2009 በጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን አፈጻጸም እንዲሁም በተያዘው በጀት ዓመት ድርጅታዊና መንግስታዊ እቅድ ላይ አባላቶቹ እየተወያዩ ነው።

የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ የጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር በማየት ቀጣይ የፖሊቲካ ስራዎችን እያቀዱ ይገኛሉ።

በድርጅቱ ህገ ደንብ መሰረት 13ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በሚቀጥሉት ወራት ያካሄዳል ተብሏል።

የ13ኛ ድርጅታዊ ጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ምርጫም በአሁኑ ስብሰባ ይካሄዳል ነው የተባለው።

እየተካሄደ ባለው ስብሰባ በክብር የተሰናበቱ ነባር የድርጅቱ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 22 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን ባካሄደው ስብሰባው በ2009 በጀት ዓመት የነበረውን የመንግስትና የድርጅቱን የስራ አፈጻጸም መገምገሙ ይታወሳል።