Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ከሙስና ተጠርጣሪዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው የ210 ግለሰቦችና ተቋማት ንብረት ታገደ


አዲስ አበባ ነሃሴ 4፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከሰሞኑ በሙስና ተጠርጥረው ጉዳያቸው በህግ እየታዩ ካሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ባለሀብቶችና ደላሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው የ210 ግለሰቦችና ተቋማት ንብረት ታገደ።

እንዲሁም 15 የተጠርጣሪዎች እና ከተጠርጣሪዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ንብረትም ታግዷል።

ከታገዱት መካከልም፦

– አሰር ኮንስትራክሽን

– ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን

– ቲና ኮንስትራክሽን

– ዲ ኤም ሲ ኮንስትራክሽን

– የማነ ግርማይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ

– ትራንስ ናሽናል ኮምፒውተር ትሬዲንግ

– ሀይሰም ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር

– ከማኒክ ትሬዲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

– ጆንግ ሊንግ ኢንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

መንግስት እያከናወነ ያለው የጸረ ሙስና ትግል ተጠናክሮ መቀጠሉም ተገልጿል።