ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በኮርፖሬሽኑ የቤቶችና የመስኖ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አቶ ኪሮስ ደስታ ከሃላፊነታቸው ከተነሱም ገና ዓመት ያልሞላቸው መሆኑም ተመልክቷል።
በተያያዘ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ለረጅም ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።
በተመሳሳይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በዚህም መንግስት በሙስና ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ነጋዴዎች እና ደላሎች ቁጥር የዛሬዎቹን ጨምሮ 51 ደርሷል።