ዘስላሰ ግደይ/መቐለ/
የሰማእታት ቀን በመጣ ቁጥር የትም ብሄድ የማንጎራጉራት የአርቲስት ሸዊት መዝገቦ ዜማ ግጥሞች ውስጥ የሚከተሉት ለወቅቱ ሁኔታ እጅግ የሚጥም ሆኖ አግኝቸዋሎህና ጥቂት ስንኞች
ሰማእታቶቻችን…ስንደክም ቀስቅሱንና አድሱን / የዜማው ርእስ/
ይመስገን ልባቹህ ህዝብን ያዳመጠ፣
ይመስገን እግራቹህ ፈንጂ የረገጠ፣
ይመስገን እጃቹህ ሀገርን ያቆመ፣
ይመስገን ጭንቅላታቹህ የህዝብ ህብረት አርቆ ስለተነበየ፣
የኦሮምያ አባገዳዎች፣ የአማራ አገር ሽማግሌዎች፣ ደቡብ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የአዲስ አበባ ተወካዮች የትግራይ የትግል ቦታዎችን በታላቅ የመታደስ መንፈስ እየተዘዋወሩ በመመልከት ላይ ሲሆኑ የቀጥታ ሚዲያ ስርጭት እንደሚሸፈን በሚጠበቀውና ሰኔ 15 በሃውልቲ ሰማእታት ስር የአበባ ጉንጉን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከታላቁ የሙስሊሞች ፆም በሀላም የተቀሩት ክልሎች ተወካዮች በተመረጠ ወቅት ተመሳሳይ ምልከታ ያደርጋሉ፡፡
መቐለ ከተማ ከገቡበት ሰኔ 12 ጀምሮ እስከ አሁን ከነበሩት ሁነቶች አስገራሚው ደደቢትን ካላየን ያሉት የአገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች እጅግ አስቸጋሪ ይእግር ጉዞ በማድረግ ለኢትዮያ የህዳሴ ጉዞ መነሻ የሆነችውን ስፍራ ሲደርሱ የነበራቸው ደስታ ልዩ ነበር፡፡
የኦሮምያ ባለሃብቶችና ህዝቡ ባዋጣው ገንዘብ ለኦህዴድ መታሰብያ ትግራይ ውስጥ ትምህርት ቤት እየተገነባ ነው
የኦሮምያ አባ ገዳዎች፣ የአማራ የአገር ሽማግሌዎች፣ የደቡብና አዲስ አበባ ተወካዮች ትግራይ ውስጥ እያደረጉ ባሉት ጉብኝት የኦሮምያ ባለሃብቶችና ህዝቡ ባዋጣው ገንዘብ ለኦህዴድ መታሰብያ ትግራይ ውስጥ ማእከላዊ ዞን ናዕዴር ዓዴት ወረዳ እየተገነባ ያለውን ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡ ናዕዴር ዓዴት ኦህዴድ የተመሰረተበት ወረዳ ነው፡፡
የኢትዮጰያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጫንቃ ተጭነው የነበሩ ገዥዎች ለማውረድ በተናጠል የተደረገው ትግል በርካታ ፈተናዎች አልፎ በኢህአዴግ መሪነት ለድል ሊበቃ የቻለው በፅናት፣ በርካታ ፈተናዎችን በማለፍና ወርቃማ ድሎችን በተከታታይ በማስመዝገብ ነበር፡፡የፅናትና ድል ተምሳሌት የሆነው ትግል ለድል የበቃበት ሚስጢር ደግሞ የኢትዮጰያውያን ጣምራ ክንድ ሊርፍበት የቻለ የመስዋእትነት ውጤት በመሆኑ ነው፡፡
በመታሰብያነት እያከበርን ያለነው የትግራይ ሰማእታት ቀን ወስደን እጅግ ውስን የሆኑ የፅናትና የድል ወቅቶች ብንጠቅስ እንኳን ትግራይ ውስጥ እጅግ መርዛማ በሆነው የናፓል ቦንብ ያልተቃጠለ ከተማና የገጠር መንደር አልነበረም፡፡ ትግሉን ለማምበርከክ ‘አሳን ለመያዝ ባህርን ማድረቅ’ በሚል ዘረኛና ፋሽሽታዊ ተግባር ይመራ የነበረው የደርግ ስርአት ለ93 ግዜ በጦር ጀቶች የትግሉ ደጀን ነው ያለውን የጭላ ከተማ ህዝብ ብቻ ከመቀጥቀጥ ጀምሮ በሃውዜን ከተማ ከተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ለገበያ የተሰበሰበን ህዝብ በመጨፍጨፍ በአንድ ጀምበር ከ2500 በላይ ህዝብ የተሰውበት ዘግናኝ ወቅቶች ታልፈፏል፡፡ እልፎች ተሰውተው እንሆ የሰማእቶቻችን ማስታወሻ እንዲሆን በቆመው ሃውልት ስር አደራቸውን ለማስቀጠል ዳግም ቃላችውን ለማደስ የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ትርጉሙ ይሀው ነው፡፡
የህዝባቸው ጭፍጨፋ እየተከላከሉ መስዋእትነት እንደ እለታዊ ምግብና ውሃ ለክቡር አላማቸው እየተሰጡ ያለፉ 60ሺ ታጋይ ሰማእታትንና ከ100ሺ በላይ አካላቸውን የገበሩ ታጋዮችም እንዲያወሳም ነው የተተከለው፡፡ ነገር ግን ሃውልታችን ደምና ስጋ ያለው ሆኖ ሁሌም የሚናገር ህያው ምስክር ማድረግ የምንችለው ለእኩልነት የተከፈለው መስዋእትነት በአንዳች ችግር እንዳይንሸራተት አጥብቀን ስንታገል መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም፡፡
ኢህአዴግ እንደ መሪ ድርጅትና መላ የኢትዮጰያ ህዝቦች በታላቅ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ውስጥ መግባታቸውም ተገቢ ነው፡፡ እንዲህ አይነት አብሮነታችን በህገ መንግስታችን ያሰርነው ቃል ኪዳን በማጠናከር የህዳሴ ጉዛችንን በተሻለ የአመለካከት ጥራትና ተግባር እንድንቀጥልበት ያደርገናል፡፡ በአንፃሩ ሀላ ቀር የሆኑት የጠባብነትና ትምክህት አስተሳሰቦች የሚጠለሉበት ስፍራ በማሳጣት የመተሳሰብ፣ የመተባበርና የልማታዊነት ግልበት እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡ እንዲህ አይነት የመታደስ መንፈስ ለማጠናከር በሰማእታት መታሰብያ ሳምንት አብራቹህን ለሰነበታቹህት የኢትዮጰያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የአገር ሽማግሌዎች ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባቹሀል፡፡