Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ብድር አገኘች


አዲስ አበባ ግንቦት 1/2009 ኢትዮጵያ ለምርታማ ሴፍቲኔት መርሃግብር የሚውል ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ከዓለም ባንክ በብድር አገኘች።

የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተወካይ ዳይሬክተር ካሮለይን ተርክ ስምምነቱን ፈርመዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ አድማሱ እንደተናገሩት፤ የብድር ስምምነቱ ለምርታማ ሴፍቲኔት መርሃግበር ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።

የብድር ስምምነቱ “በድርቅ የተጎዱና በኑሮ የተጎሳቆሉ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል” ነው ያሉት።

የምርታማ ሴፍቲኔቱ ተጠቃሚ የገጠር ነዋሪዎች በጥሬ ገንዘብ ወይም በምግብ መልክ እንደሚሰጣቸው ነው የተመለከተው።

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተወካይ ዳይሬክተር ካሮለይን ተርክ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ የብድር ስምምነቱ በምርታማ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ይውላል።

ባንኩ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ በምርታማ ሴፍቲኔት መርሃግብር የሚሰጠው ድጋፍ ያጠናከረ ሲሆን፤ ይህ የብድር ስምምነት የመርሃግብሩ አራተኛውን ምዕራፍ ለማስፈፀም የሚውል መሆኑ ታውቋል።

የምርታማ ሴፍቲኔት መርሃግብር በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ በኑሯቸው ለውጥ እንዲያመጡ ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች በራስ አቅም ከጉዳት ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል።

ባንኩ መንግሥት ለሚያደርገው ጥረት የሚሰጠው ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።