Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የትግራይ ክልል በኦሮሚያ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ አደረገ


አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በድርቅ የተጎዱ የቦረና እና ጉጂ ዞን አርብቶ አደሮችን ለመደገፍ የትግራይ ክልል በ15 ተሽከርካሪዎች የተጫነ የእንሰሳት መኖ ድጋፍ በቦታው በመገኘት አስረክቧል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወይዘሪት ኡሚ አባጀማል፥ የትግራይ ክልል ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፥ የሁለቱ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በጥሩ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም አጋጣሚ የሚቀጥል መሆኑን ክልሉ ያደረገው ድጋፍ ያሳያል ብለዋል።

የትግራይ ክልል ያደረገውን ድጋፍ ያስረከቡት የክልሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ጌታቸው ፈረደ በበኩላቸው፥ “ያደረግነው ድጋፍ በቂ ባይሆንም ሁሌም አብረናችሁ እንዳለን የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

ከሳምንት በፊት የአማራ ክልል 5 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል እና ሁለት የውሃ ቦቴ ተሽከርካሪዎችን ለኦሮሚያ ክልል ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።