Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢትዮጵያና ቻይና በጤና ዘርፍ ተባብረው ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ህዳር 23፣ 2009

ኢትዮጵያና ቻይና በጤና ዘርፍ ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ተፈራረሙ።
%e1%8a%a5%e1%89%b2%e1%89%bb%e1%8b%ad%e1%8a%93
ስምምነቱ በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ የህክምና ተቋማትን መሳሪያዎች በሟሟላት፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታና ከአደጋ ጋር የተያያዙ የህክምና አገልግሎት ሰጪ ተቋም ለመመስረት ድጋፍ ማድረግን የሚያካትት ነው።

በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃኔ ሲፈርሙ በቻይና በኩል ደግሞ የጤና እና የቤተሰብ ምጣኔ ዕቅድ ኮሚሽነር ዋንግ ፔያን ፈርመዋል።

ከአደጋ ጋር የተያያዘ የህክምና አገልግሎት መስጫ በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አከባቢ እንደሚቋቋም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ይህም ከአደጋ ጋር የተያያዘ የህክምና አገልግሎት መስጫ ሲገነባ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ያደርግዋል።

ስምምነቱ ቻይናውያን ሙያተኞችን ወደ አገር ውስጥ ከማስገባት ባለፈ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ለተጨማሪ ሥልጠና ወደ ቻይና በመላክ አገሪቱ ያላትን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።