የትግራይ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ሰኞ ያካሂዳል
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን የፊታችን ሰኞ ህዳር 26 ቀን ሊያካሂድ ነው።
ምክር ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ በአስቸኳይ ጉባኤው አዳዲስ ሹመቶች ለምክር ቤቱ ቀርበው ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እንደዚሁም ምክር ቤቱ ተመልክቶ እንዲያፀድቃቸው አዳዲስ አዋጆችም የሚቀርቡ ይሆናል ነው የተባለው።