ህዳር 12፣ 2009
ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ናይጀሪያ የአፍሪካ የፋይናንስ ማዕከላት እየሆኑ መምጣታቸውን የአፍሪካ ቢዝነስ ትራቭል አሶሴሽን አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ዕድገት ተመራጭ መዳረሻ መሆኗን የአፍሪካ ቢዝነስ ትራቭል አሶሴሽን መስራች ሞኒክ ስዋርት ገልጻለች፡፡
በተጨማሪም የናይጀሪዋ ሌጎስ እና የሩዋንዳዋ ኪጋሊ የአፍሪካ ፋይናንስ ማረፊያ የሆኑ ከተሞች መሆናቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ እና የሩዋንዳ ቱሪዝም ዕድገት ለማዕከልነታቸው ከፍተኛ ሚና መጫወቱን በዘገባው ተገልጿል፡፡
ኬንያ፣ ሴኔጋል እና ቡርኪናፋሶም በፋይናንስ ማዕከልነት ከተቀመጡ ሀገራት ቀጣዮቹን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ደቡብ አፍሪካ በአህጉሩ የግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት ተርታ ብትመደብም የአህጉሩ የፋይናንስ ማዕከል ያለመሆኗ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
የአፍሪካ ትራቭል አሶሴሽን የአፍሪካን የፋይናንስ ገጽታ ላይ አትኩሮ ጥናት የሚያወጣ ተቋም ነው፡፡