Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

አንጌላ ሜርክል የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል

engela-mark
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀምረዋል።

መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ማምሻውን ነው አዲስ አበባ የገቡት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አንጌላ ሜርክል በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙንት ዙሪያ ይወያያሉ።

በውይይታቸውም ለረጅም ዘመናት የቆየውን የሁለቱን ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት የሚያጠናክሩ አጀንዳዎችን ያነሳሉ።

መሪዎቹ በሰላምና ጸጥታ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በስደትና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መራሂተ መንግስቷ በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ቆይታ በአፍሪካ ሃገራት ስላለው ስደትና ፍልሰት ጉዳይ ከአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።

በአዲስ አበባ በጀርመን የገንዘብ ድጋፍ የተሰራው የአፍሪካ ስላም እና ፀጥታ ማዕከልም መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በተገኙበት ይመረቃል።