Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በ10 ቢሊዮን ብር የወጣቶች ተንቀሳቀሽ ፈንድ ሊቋቋም ነው

መስከረም 30፣2009
የወጣቶች ተንቀሳቀሽ ፈንድ ለሚቋቋም 10 ቢሊዮን ብር መመደቡን የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አስታወቁ፡፡
parlama-one-pic
ፕሬዝዳንቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሁለተኛ አመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ስነ ስርአት ሲከፍቱ እንዳሉት  2009 ዓ.ም የአገሪቱን ወጣቶች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ  አብይት ኩረት እንደሚሆን ተናግረዋል። ለዚህም  ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ወረዳዎች የወጣቶች ተንቀሳቃሽ ፈንድ ይሰጣሉ ለፈንዱ ማቋቋሚያም 10 ቢሊዮን ብር ተመድቧል ብለዋል፡፡
ፈንዱ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ እንደሚሆን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። የሥራ ፈጠራ የሚያተኩርባቸው መስኮች ተለይተውና ከወጣቶች ጋር ተመክሮባቸው ወደ ትግበራ እንደሚገባም አመልክተዋል።
ፕሬዝዳንቱ መንግሥት ከወጣቶች ፈንድ አጠቃቀምና የፕሮጀክቶች ትግበራ መሰረተ ሃሳቦችን ከወረዳ አመራርና ከወጣቶች ጋር በመመካከር እንደሚያስፈጽም ገልጸው ሂደቱ በየጊዜው እየተገመገመ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።
ወጣቶች የራሳቸው ፍትሃዊ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፍላጎትና ጥያቄዎች ያሏቸው በመሆኑ ጥያቄዎችን አስተሳስሮ መፍታት እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡ እንደወጣቶች ሁሉ የሲቪል ሰርቪሱን እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግር ለመቅረፍ የደሞዝ ማስተካከያና ሌሎች ስራዎች ይሰራሉም ብለዋል፡፡
ባለፈው አመት በታየው የፖለቲካ ቀውስ በርከት ያሉ ወጣቶች መሳተፋቸው ለጉዳዩ ትኩረት እንዲስጥ ማድረጉንም ተናግረውዋል።