አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር ህገመንግስታዊ ስርአቱን በማክበር ልዩነቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማማ።
የግንባሩ የጦር ክንፍ ዋና አዘዥ ቶት ፓልቾይ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማክበር ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
የጦር አዛዡ በዛሬው እለት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተወያይተዋል።
የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር በአሁኑ ስዓት የተለያዩ አካላት መጠቀሚያ ሆኗል ያሉት አዛዡ፥ ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማክበር ለመንቀሳቀስ በመስማማት ለዚሁ ውሳኔ መብቃታቸውን ገልፀዋል።
በኤርትራና በሱዳን ድንበር ያሉ የግንባሩን አባላት ወደሀገር ለማስገባትም እንቅስቃሴ ተጀምሯል ማለታቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።