ግጠም አለኝ ሲለኝ ጣልያን መጣ ብየ፣
ግጠም አለኝ ሲለኝ ድርቡሽ መጣ ብየ፣
ግብጽ ወይም ቱርክ ይሆናሉ ብየ፣
ዝናሬን አስጥሜ ነፍጤን ወላውየ፣
ቀና ስል ልራመድ አረ ጎራው ብየ፣
ለካስ ግጠም ያለኝ ከወንድሜ ጋር ነው፣
ከዛ በቁርጥ ቀን የማይጠፋ ጀግናው፣
ከትግራይ ህዝብ ጋር ኢትዮጵያዊ አርበኛው።
ጉድ በል ጎንደሬ በነዚህ ነውረኞች፣
አገር በሚያምሱ ሆዳሞች፣
አረ ንገራቸው ይወቁ ቁርጣቸው፣
ዘፈን ቀረርቶና ሽለላቸው፣
ሌማልሞን እንደማያሻግራቸው፣
አረ ጮክ ብለህ በደንብ ንገራቸው፣
ከኮማሪቷ ቤት ከጎረቤታቸው፣
እንዲገዘግዙ ማሲንቋቸው፣
በደምብ ንገርልኝ እስኪገባቸው፣
ማንም እንደሌለ የሚለያያቸው፣
ትግሬና ጎንደሬ ኢትዮጵያዊን ናቸው፣
አልሰማህም ካለ ግን ይህንን ከርሳሙ፣
ላከው ወደ ፈለገው ወዳጅ ዘመድ ይስሙ፣
ያኔ ይማራታል ሲደፋ በአፍ ጢሙ።
እማታበቅለው የላት ውዲቷ አገሬ፣
አረሞች በዝቷል ጉድ በል ጎንደሬ!
One Response to ጉድ በል ጎንደሬ