የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ
I. መግብያ፡-
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 3-5 ያካሄደዉን ኣስቸኳይ ሰብሰባ ኣጠናቋል። ህወሓት/ኢህወዴግ በ17 ዓመቱ የትጥቅ ትዓልም ሆነ ሩብ ክፍለ ዘመን ባለቆጠረው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ትግል ምዕራፎች ሁሉ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረግነው ትግል በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፈን እዚህ ላይ መድረስ ችለናል። የ43 ዓመታት የድልና የፅናት ጉዞአችን ስኬት ምንጭ የጠራና ብቁ አብዮታዊ መስመር ይዞን የዘለቅን መሆኑ ነው። ይኸንን መስመር በፅናት ጨብጦ በፅናት ታግሎ የሚያታግል ድርጅት ባለቤት ስለሆንን ነው። ባለፉት 27 ዓመታት ባጠቃላይ፣ ባለፉት የ17 የተሐድሶ ዓመታት ደግሞ በተለይ ዙርያ መለስ መሰረታዊ ለውጥ መስመዝገብ ችለናል። ሃገራችን ኢትዮዽያ የነበረችበት እጅግ ኣስፈሪ የመበታተንና የማሽቆልቆል ጉዞ ተገቶ ወደ ኣዲስ ምዕራፍ እንድትሸጋገርና ስሚና ክብር ከፍ ብሎ እንዲጠራ ኢህኣዲግ እልህ አስጨራሸ ትግል ኣካሂዷል። በተደረገዉ ትግል የሃገራችን ህዝቦች የመልማት እኩል ዕድል ያረጋገጠ ስርዓት ተገንብቶ ህዝቦችን በኢኮኖሚና በማሕበራዊ ረገድ ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ዉጤት ለማረጋገጥ ተችሏል። በእርግጥም አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን ሃገራችንን ከጥፋት የታደገ፣ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠበት አዲሲቷ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮዽያ እንድትፈጠር ያደረገና ለወዲፊትም የሃገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ መሆኑ የአስከኣሁኑ ትግላችን ያረጋገጠው እውነት ነው።
ይኸ ተኣምር የፈጠረና የሃገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ የሚያስችል ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኣደጋ ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ እንዲፈጠር ከምንም በላይ የመሪ ድርጅታችን ኢህኣዴግ አመራር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ባህርይው እየተሸረሸረ በከፋ የጥገኛ ዝቅተት ኣረንቋ ውስጥ በመዘፈቁ መሆኑን ድርጅታችን ኢህአዴግ በሚገባ የተነተነዉ ጉዳይ ነዉ። ይሁን እንጂ ይኸንን ፈተና በሚገባ ለማለፍ ሲባል በድርጅታችን የተጀመረዉ በጥልቅ የመታደስ እንቅስቓሴ ኣሁንም ቢሆን በሚፈለገዉ ደረጃ ሊሳካ ኣልቻለም።
ይህንን መነሻ በማድረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በወሰናቸዉ ዉሳኔዎች በሃገራችንና ክልላችን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ የትግል አቅጣዎቻችን ላይ በዝርዝር በመውያየት ውሳኔዎች አስልፏል።
II. ውሳነዎች
ሀ. የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ግንቦት 28/2010 ዓ.ም ባካሄደዉ አስቸኳይ ሰብሰባ የኢትዮ-ኤርትራን ግጭት በሰለማዊ መንገድ ለመፍታትና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን አስመልክቶ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ የቀረበለት ሪፖርት በዝርዝር በማየት የሚቀጥሉትን ውሳኔዎች አሰልፏል።
1. ከምንም ነገር አስቀድሞ የኢህአዴግ ስራ ኣስፈፃሚ ሊያየው ይገባ የነበረዉ ጉዳይ የኢህአዴግ ምክርቤት በመጋቢት /2010 ዓ.ም ያስቀመጠዉን ወሳኔና ግምገማ መሰረት በማድረግ በድርጅታችን በግልጥ እየታየ የመጠዉን መሰረታዊ የአመራር ብልሽትና ያስከተለዉን ጉዳት፣ እንዲሁም ባለፈዉ የተጀመረዉ የጥልቀት መታደስ የደረሰበት ደረጃን በጥልቀት በመገምገም በሃገራችን ዋነኛ ችግር ላይ ትኩረት ኣድርጎ ማየት አለመቻሉ አንድ መሰረታዊ ጉድለት ነው።
2. የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ማየት የነበረበት ሌላ መሰረታዊ ጉዳይ አሁን ገጥሞን ላለው መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ ላይ ትኩረት ኣድርጎ መውያየት መሆን ሲገባዉ የችግሩ ባስከተላቸው ውጤቶችና ለጊዚያዊ መፍትሔዎች ቅድሚያ መስጠቱ አንድ ሌላ ጉድለት እንደ ሆነና፣ ዘለቂው መፍትሔ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመራችን በግልፅ የለያቸውን የልማት አቅምቻችን ማለትም መላው ህዝባችን፣ መንግስትና የግል ባለሃብቱን በማደራጀት ርብርብ እንዲያደርጉ መቻል ላይ ያለብን ችግር ላይ ትኩረት ስጥቶ መውያየት ኣልቻለም።
3. እነዚህ እላይ የጠቀስናቸው ጉድላቶች እንደ ተጠበቁ ሆነው ስራ ኣስፈፃሚው የኢትዮዽያና የኤርትራን ጉዳይ ኣስመልክቶ የወሰነው ውሳኔ በመሰረቱ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ በኢህአዴግ የሚመራዉ መንግስት ለኣፍሪካ ቀንድ ሰላም በጠቃላይ ለሁለቱ ሃገራት ወንድማሞች ህዝቦች በተለይ ሲባል ስምምነቱን ያለቅድመ ሁኔታ በመቀበል ህዝባችንና መላዉ ኣበላችንን በማወያየትና በማሳመን እንድሁም ዓለም ኣቀፉን ማሕበረሰብ ከጎኑ በማሳለፍ ለተግባራዊነቱ ያላሰለሰ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት 18 ዓመታት ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ አልተቻለም። ስለሆነም የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሳለፈዉ ዉሳኔ በመሰረቱ ከሰላም ፖሊስያችን ጋር የተጣጣመ መሆኑን በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ዉሳኔ መተላለፉ ተገቢና ዉቅታዊ መሆኑን የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ደምድሟል።
ኣፈፃፀሙን በሚመለከት ግን ሃገራችን ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ጋር ከሏት የአዋሳኝ ድንበር ጉዳዮች አንፃር ጭምር እጅግ ከፍ ያለ ትርጉም ያለዉ በመሆኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባዉ አፅንኦት ሰጥቶ ተውያይቷል። ከዚህ ጋር በተያየዘ በኢትዮ-ኤርትራ አዋሳኝ አከባቢዎች የሚኖረዉ ህዝብና ሚሊሻ ላለፉት 20 ዓመታት ከኑሮኣቸዉና ከሥራቸው ተፈነቅለዉ የሃገራችንን ልዓላዊነትና ህገ-መንግስታችን ለማሰከበር ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም ለሳዩት ቆረጥነትና ከከፈሉት የማይታመን መስዋዕትነት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ያለዉን ክብርና ኣድናቆት እየገለፀ ድርጅታችን ኢህአዴግና ከፌደራል መንግስት ጋር በመሆን በቂ ድጋፍ ሊያገኙ እንዲሚገባ ወስኗል።
4. የኢህኣዴግ ስራ ኣሰፈፃሚ ኮሚቴ አሁን የገጠመንን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል ከመንግስት የልማት ድርጅቶችን መካከል ቴሌ፣ ኤለክትሪክ ማመንጨዎች፣ ሎጀስቲክስና የኢትዮዽያ ኣየር መንገድ ከፍተኛዉ ድርሻ በመያዝ የግል ባለሃበቶችን ለማሳተፍ እንዲሁም የቀሩትን የልማት ድርጅቶች በከፊል ወይም በሙሉ ወደ ግል ይዞታ ለማስተላለፍ የወሰነዉ ውሳኔ ከፕሮግራማችንና ፖሊስዎቻችን ጋር የማይጋጭ፣ ባለፉት ጉባኤዎቻችን እየተወሰነ የመጣና ወቅታዊ መሆኑን በማረጋገጥ ተቀብሎታል። ይሁን እንጂ ኣፈፃፀሙ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲዳረግና ልማታዊ ዴሞከራሲያዊ መስመራችንንም ሆነ የኢትዮዽያ ህዝቦችን ጥቅም በማይጎዳ መልኩ መከናወን እንዳለበት አፅንኦት ሰጥቶበታል።
5. በኢትዮ-ኤርትራ ዘላቂ ሰላም ጉዳይም ሆነ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር በተያየዘ የተወሰኑ ውሳኔዎች ወደ ኢህአዴግ ምክርቤት ሳይቀርቡ፣ አጋር ድርጅቶች ሳይሳተፉበት እና የሚመልከታቸው አካላት በዝርዝር ሳይወያይበት እንደመጨረሻ ውሳኔ ተወስዶ ለህዝብ ይፋ መደረጉ አንድ ጉድለት እንደሆነ ማእከላዊ ኮሚቴዉ ደምድሟል።
6. የኢትዮዽያ በሔር፣ በሄረሰቦችና ህዝቦች ከዳር እስከዳር በከፍተኛ ሃገር ፍቅር የተሳተፉበት እና መስዋእት የከፈሉበት ጉዳይ በዝርዝር ሳይወያዩበት እና በቂ መተማመን ሳይደረስበት በሚድያ ይፋ መግለጫ መሰጠቱ ህዝባችን ላይ ቅሬታ፣ ቁጣና መደነጋገር የፈጠረ በመሆኑ አንድ ሌላ ጉድለት ነው።
ለ. የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በጥልቀት ከተወያየባቸው ጉዳዮች አንዱ አሁን ያለንበት ክልላዊ እና ሃገራዊ ሁኔታ እንዲሁም ቀጣይ የትግል አቅጫጫዎች የሚሚለከት ነው። በኢህኣዴግ ደረጃም ሆነ በህወሓት ካለፉት አመታት ጀምሮ ልማታዊ መስመራችን እና በህገመንግስታችን ላይ ያጋጠመ ያለዉን ችግር ሲገምግም ቆይቷል። ይሁን እንጂ የችግሮቹ ስፋትና ትርጉም በኢህአዴግ ደረጃ በጥልቀት መገምገም እንዳለበት በመግባባት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።
1. የኢህአዴግ ምክርቤት በመጋቢት 2010 ባስቀመጣቸው ውሳኔዎች ድርጅታችንን ከአደጋ ለማዳን እንዲቻል የለየናቸው ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው በጥብቅ ድስፕሊን እና ተጠያቅነት እንዲተገበሩት ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጧል። በዚ ረገድ በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴው የደረሰበት ደረጃ በኢህአዴግ እንዲገምገም የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ይጠይቃል።
2. በዴሞክራሲ ሓይሎች እና በጥገኝነት መካከል የሚደረገው ቀጣዩ የትግል ምእራፍ በዋናነት በዴሞክራሲ እና በልማት ዙርያ በሚለኮስ ንቅናቄ ማሕበራዊ መሰረታችን እና ከልማታችን ተጠቃሚ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሚያደርጉት የተደራጃ ትግል ነው። ይህን ለማድረግ እንዲቻል መላው ህዝባችን እና አባላችን የምንገኝበትን መድረክ ባህሪ መነሻ በማድረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በሃገር ደረጃ በሚደረገው ሁሉንአቀፍ ትግል በቁርጠኝነት እንዲረባረብ ወስኗል።
3. በአሁኑ ወቅት በኢህአዴግ ደረጃ እየተደረጉ ያሉ የኢህአዴግን ህገ-ደንብ እና ተቋማዊ አስራር ያልተከተሉ የአመራር ምዳባዎች እንዲታረሙ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ይጠይቃል።
4. ለደርጅታችን ነባር አመራሮች እውቅና እንዲሰጥ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ወስኗል።
5. በሃገራችን ህገ መንግስት በሚገባ መልስ የሰጠባቸው የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎችን ፈደራላዊ ስርዓታችን በመፃረር እና የህዝባችን ክብር በሚነካ መልኩ በሓይል እና በተፅእኖ የትግራይ እና ህዝብ አድነት እና ሰላም ለመረበሽ የተደረጉ ያሉት ፀረ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሶች ህወሓት ከህዝቡ ጋር በመሆን በፅናት ለመታገል ወስኗል።
6. የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት እንደለፈው ግዜ ሁሉ የአብያታዊ ዴሞከራሲያዊ መስመራችን አስተማማኝ ደጀን በመሆን ትግላችንን የሚጠናክር እና እንደ ካሁን ቀደሙ በመሰመራችን ዙርያ ጠንካራ ርብርብ እንዲደረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ወስኗል።
7. ከህዝባችን ጋር ባለፉት ጥቅት ወራት ባካሄድናቸው መድረኮች በርካታ ችግሮች እንዳሉ ተገንዝበናል። ድርጅታችን የነዚህ ችግሮች መነሻ እንዲሁም የመፍትሔ ኣቅጫጫ በግልፅ ኣስቀምጦ በተግባር ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሌትተቀን ርብርብ ለማድረግ ወስኗል።
8. ህዝባችን መሪ ድርጅቱ እንዲታደስ በተለያዩ መድረኮች ያደረገዉ ተሳትፎ እና ትግል ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ባህሪውን ጠብቆ እንዲሄድ ላረገው አስተዋፅኦ ማእከላዊ ኮሚቴው አድናቆቱን እየገለፀ፤ በቀጣይም ቢሆን ትግሉን በተደራጀ መልኩ እንዲ ቀጥል ጥሪውን ያቀርባል። በዚህ አጋጣሚ ሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ ተከትለው ኣማራጭ ሃሳብ ከሚያራምዱ ሓይሎች ጋር ኣብሮ ለመስራት ያለው ዝግጅነት መግለፅ ይወዳል። ይሁን እንጂ ህወሓት እና የትግራይን ህዝብ ለማዳከም እና ለመምታት በተለያዩ መንገዶች ፀረ ትግራይ ህዝብ እና ፀረ ህወሓት እንቅስቃሴ የሚያድርጉ የውስጥም የውጭም ሓይሎች ህዝቡ ኣምሮ እንዲታግላቸው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል።
9. ወቅታዊ ሁኔታዉን በፍጥነት ለማየት እና ለመገምገም የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ እና ምክርቤት አስቸኳይ ሰብሰባ እንዲጠራ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ይጠይቃል።
ህገ መንግስታችና ህገ መንግስታዊ ስርአታችን ለማጠናከር እንረባረብ!!
ዘለአለማዊ ክብርና ሞጎስ ለትጉሉ ሰማእታት!!
የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ
ሰነ 06/2010 ዓ.ም
መቐለ፤