አዲስአበባ፣ ግንቦት፣ 11 2010(ኤፍቢሲ)ሼህ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ በቅርቡ እንደሚፈቱ እና ከሳዑዲ አሪቢያው አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር ከስምምነት ላይ እንደተደረሰ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሚሊንየም አዳራሽ በማይንድሴት ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር በሳዑዲ አረቢያ በነበረቸው ቆይታ ከሀገሪቱ አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር ሼህ ሙሀመድ አላሙዲን እንዲፈታ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ገልፀዋል።
የሼህ ሙሀመድ አላሙዲን ዛሬ ወደ ሀገር ቤት ይዞ ለመምጣት አስበው እንደነበር እና በጊዜያዊ ችግር ያንን ማድረግ እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሼህ ሙሀመድ አላሙዲን የሚፈቱበትን ቀን ባይቆረጥም በቅርቡ እንደሚፈቱ አረጋግጠዋል።
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችም የሼህ ሙሀመድ አላሙዲን ጉዳይ የራሳቸውን ጉዳይ ማድረግ እንዳለባቸውምበ እና የሁሉም ጉዳይ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
በሳዕዲ አረቢያ ቆይታቸው 1 ሺህ ኢትዮጵያውያን እንደተፈቱ የገለፁ ሲሆን ከፊሉ ከዛሬ ምሽት ጅምር ወደ ሀገራቸው እንደሚገቡ ተናግረዋል።