Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ጀርመን የጥላቻ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ማህበራዊ ሚድያዎችን እስከ 50 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት ልትጥልባቸው ነው


ጀርመን በማህበራዊ ሚዲያ የሚወጡ መረጃዎች ጥላቻ ንግግሮች ያካተቱ ሆነው ሲገኙ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስገድድ ህግ ከዚህ ቀደም ማውጣቷ ይታወቃል፡፡

ለዚህም ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ይረዳቸው ዘንድ እስከ ተሸኘው የአውሮፓ አመት ድረስ ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ አዲሱ የ2018 አውሮፓዊያን መግባቱን ተከትሎ የጀርመን መንግስት አዲስ ያወጣውን ህግ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

በህጉ መሰረት ማህበራዊ ሚዲያዎች የጥላቻ ንግግር መያዛቸው በተነገራቸው 24 ሰዓት ውስጥ ማስወገድ ይኖርባቸዋል፡፡

ነገር ግን ሚዲያዎቹ ይህን ሳያደርጉ ቢቀር እስከ 50 ሚሊዮን ዩሮ መቀጮ ይጣልባቸዋል ተብሏል፡፡

በዚህ ህግ 2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያላቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች አዲስ በሚወጣው ህግ ይዳኛሉ፡፡

ፌስ ቡክ፣ ቲውተር፣ ዩቱዩብ እና መሰል ማህበራዊ ሚዲያዎች በህጉ ትኩረት የሚሰጣቸው አካላት ናቸው፡፡

የጀርመን መንግስት ይህ ህግ ተጥሶ ሲገኝ ዜጎች የሚያሳውቁበት መጠይቅ በኦላይን ማሰራጨቱን ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ የጥላቻ ንግግር ሆኖ ሲገኝ እንዲወገድ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ማህበራዊ ሚዲያዎች አሁን እየሰጡት ካለው የመልስ ጊዜ ጋር ሲነፃጸር በጣም አጭር ጊዜ መሆኑ እየተገለፀ ነው፡፡