Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የአቶ በረከት ስምዖንን የስራ መልቀቂያ ጥያቄን መንግስት ተቀበለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ክህዝብ ተወካዮች ምክር አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት

ምላሽ አቶ በረከት ስምኦን የመልቀቂያ ጥያቄ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑን ተናግረዋል።

አቶ በረከት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ መንግስት ውሳኔያቸውን እንደተቀበላቸው ነው የገለጹት።

አቶ በረከት ስምዖን ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊነት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ነባር የኢህአዴግ አመራር ናቸው።

ቀደም ሲል የማስታወቂያ ሚኒስትር እና የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት አቶ በረከት፥ የስራ መልቀቂያ እስካስገቡበት ጊዜ ድረስ በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።

በሌላ በኩል የአቶ አባዱላ ገመዳ የመልቀቂያ ጥያቄ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበ በመሆኑ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ተናግረዋል።