አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ በረከት ስምዖን ከስራ ሀላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸውን መንግስት አረጋገጠ።
የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጡት፥ በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል
ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ከሀላፊነታቸው ለመነሳት ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ አስገብተዋል።
የአቶ በረከት ጥያቄንም መንግስት እየተመለከተ መሆኑን ነው የገለፁት።
አቶ በረከት ስምዖን የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡበት ምክንያት ግን አልታወቀም።