Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በቁጥጥር ስር ዋሉ

አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል


አቶ ዓለማየሁ ጉጆ


አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 28፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ደስታ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በኮርፖሬሽኑ የቤቶችና የመስኖ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አቶ ኪሮስ ደስታ ከሃላፊነታቸው ከተነሱም ገና ዓመት ያልሞላቸው መሆኑም ተመልክቷል።

በተያያዘ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ለረጅም ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

በተመሳሳይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም መንግስት በሙስና ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ነጋዴዎች እና ደላሎች ቁጥር የዛሬዎቹን ጨምሮ 51 ደርሷል።