Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ጠ/ሚ ሀይለማርያም በኡጋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረግ ጀመሩ


አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ ኡጋንዳ ገብተዋል።

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒን ጨምሮ በርካታ የአገሪቱ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ከፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ጋር በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በመምከር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

መሪዎቹ የከተነጋገሩባቸው እና ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከል በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ በቀጣይ በጋራ መስራት ይገኝበታል።

እንደዚሁም ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት በምትመራው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ በኩል ደቡብ ሱዳንን ለማረጋጋት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በሶማሊያ ለተረጋጋ መንግስት መኖር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ መሰረተ ልማቶች እና ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲስፋፉም በጋራ የበኩላቸውን መስራት ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።

“ኢትዮጵያ እና ኬንያን የሚያገናኘውን መንገድንም በመጠቀም የንግድ ግኑኝነታችንን ለማሳደግ እንሰራለንም” ብለዋል።

አገራቱ በወታደራዊ መስክም ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ነው የተስማሙት።


ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም በቆይታቸው ነገ አንድን የንግድ እርሻ የሚጎበኙ ሲሆን፥ ቅዳሜ እለት ደግሞ አንድን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ይጎበኛሉ።