Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ሴቪታል ኩባንያ በኢትዮጵያ የቅባት እህሎችና የሸንኮራ አገዳ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው


መጋቢት 13/2009 የአልጄሪያው ግዙፉ ሴቪታል ኩባንያ በ360 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮዽያ የቅባት እህሎችና የሸንኮራ አገዳ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።

የሴቪታል ካምፓኒ ሃላፊ ኢሳድ ረብራብ ለስብሰባ ጄኔቫ በተገኙበት ወቅት ስለ ጉዳዩ ቃለ መጠይቅ ላደረገላቸው የሬውተርስ ዘጋቢ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

“ለጅቡቲ ወደብ ከምናደርገው የሎጂስቲክስ ወጪ ባሻገር በኢትዮዽያ በጠቅላላው 360 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት እናደርጋለን።” ብለዋል።

ሃላፊው ከኢትዮዽያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ እና ከጅቡቲው የወደብና ነፃ የንግድ ቀጣና ባለስልጣን ሊቀመንበር አቡባከር ኦማር ሃዲ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተነጋግሯል።

ሴቪታል 3ነጥብ5 ሚሊዮን ቶን የቅባት እህሎችን የማቀነባበር አቅም ያለው ፋብሪካ እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ቶን የሸንኮራ አገዳና 750,000 ቶን የአትክልት ዘይት ማቀነባበሪያን ጨምሮ ምርቶቹን የሚሸጥባቸው ተቋማት የመገንባት ዕቅድ ይዟል።

“በአልጄሪያ ያካበትነውን ልምድና ዕውቀት ተጠቅመን ኢትዮዽያውያን ወዳጆቻችን ኢንቨስት ከምናደርገው ገንዘብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንፈልጋለን።”በማለት ረብራብ ተናግረዋል።

ሃላፊው ፕሮጀክቱ መቼ ወደ ተግባር እንደሚገባ ግልፅ ያላደረጉ ሲሆን በትብብር ሊሰሩ የሚችሉ ባንኮች ካሉ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል ዘገባው አመልክቷል።