Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የከተራ በዓል ዛሬ በድምቀት ይከበራል


አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተራ በዓል ዛሬ በመላ ሀገሪቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች በድምቀት ይከበራል።

ዛሬ ከ8 ስዓት ጀምሮ ታቦታት በምእመናን ታጅበው ወደ ታቦት ማደሪያ ስፍራዎች ይወርዳሉ።

የከተራ እና የጥምቀት በዓል በተለይም በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቴያስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ምእመናን፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች እና በርካታ ቱሪስቶች በተገኙበት በሀገር አቀፍ ደረጃ በጃን ሜዳ ይከበራል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሃንስ እጅ ለመጠመቅ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ የወረደበትን እለት ለማሰብ የሚከበር ነው።

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ቀኖና መሰረት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከምታከብራቸው ዘጠኝ አብይ በዓላት መካከል አንዱ ጥምቀት ነው።

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን የሚያከብሩትም ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በ30 አመቱ የማዳን ስራውን በጥምቀት የጀመረበትን ጊዜ ለማስታወስ እንደሆነም ቤተ ክርስቲያኒቱ ትገልፃለች።

የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጊዜ በዋዜማው ታቦታቱ ከየቤተ ክርስቲያናቱ ወጥተው በወንዝ ዳር ወይም በሰው ሠራሽ የውሃ ግድብ ዳር በዳስ፣ ድንኳን እንደሚያድሩም አቡነ ጎርጎርዮስ በፃፉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ታሪክ መፅሃፍ ላይ ሰፍሮ ይገኛል።

ሌሊትም ቅዳሴ የሚፈፀም ሲሆን፥ ሲነጋ በባህረ ጥምቀቱ ፀሎተ አኩቴት ተደርሶ አራቱም ወንጌላት ከተነበቡ በኋላ ውሃው ተባርኮ ለተሰበሰበው ህዝብ ተረጭቶ ጥምቀት ይፈጸማል።