Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በመቀሌ-ወልድያ-ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የ2 ዋሻዎች ቁፋሮ ተጠናቀቀ


አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመቀሌ-ወልድያ-ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ላይ ቁፋሯቸው እየተከናወኑ ካሉ ስምንት ዋሻዎች ውስጥ እያንዳንዳቸው ሁለት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የሁለት ዋሻዎች ቁፋሮ ተጠናቋል።

የኩክኒ የዋሻዎች ናቸው ግንባታቸው የተጠናቀቀው።

በዚህ የባቡር ፕሮጀክት ላይ ካሉት ዋሻዎች በርዝመቱ ቀዳሚ የሆነው የማይሰልፊ ዋሻ ከ2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር በላይ ተጠናቋል።

ዋሻው በአጠቃላይ 3 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዲኖረው ተደርጎ እይተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

የዚህ ዋሻ መጠናቀቅ ለፕሮጀክቱ መፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው የፕሮጀክቱ ሀላፊ ገብረመድህን ገብረአሊፍ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹ ዋሻዎች ለመጠናቀቅ ከ20 እስከ 25 ሜትር ግንባታ ይቀራቸዋልም ብለዋል።

የባቡር መስመሩ 44 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ከ170 በላይ አነስተኛና እስከ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ድልድዮች ይኖሩታል።

አሁን ላይ የድልድዮቹ አብዛኛ ምሰሶዎች ተሰርተዋል።

የመቀሌ-ወልድያ-ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጭ በቻይናው ሲሲሲሲ ኩባንያ የሚከናወን መሆኑ ይታወቃል ።