ምስራቅ አፍሪካን በኢንተርኔት ለማስተሳሰር የ100 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
የጅቡቲ አፍሪካ ሪጅናል ኢክስፕረስ የተሰኘው ይኸው ፕሮጀክት 4700 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።
ይኸው በባህር ውስጥ ለውጥ የሚዘረጋው የኢንተርኔት ፕሮጀክት በምስራቅ አፍሪካ መንግስታትና ቴሌኮም ድርጅቶች ትብብር ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል።
የባህር ውስጥ የኢንተርኔት መስመር ዝርጋታው ኬንያን፣ ጅቡቲን፣ የመንና ሶማሊያን ዋነኛተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል።