አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የቀረበውን ሹመት አጸደቀ።
ምክር ቤቱ የስድስት የቢሮ ሀላፊዎች፣ የክልሉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የክልሉ ዋና ኦዲተር ኮሚሽነርን ሹመት ነው ያፀደቀው።
የክልሉ ርዕስ መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ ሹመቱን ባቀረቡበት ወቅት፥ በክልሉ በየደረጃው በተደረጉ በጥልቅ የመታደስ ንቃናቄዎች መሰረት ሹመቱ መቅረቡን ተናግረዋል።
በተሃድሶው መሰረትም ህዝብን በልማት ለመካስ እና የመልካም አስተዳደር እርካታ ለመፍጠር ይሰራል ነው ያሉት።
አዲስ ተሿሚዎቹ አመራሮች ሙያዊ ብቃታቸው፣ በየትኛው ዘርፍ ቢሰማሩ ውጤታማ ይሆናሉ የሚለውና የምሁራንን ተሳትፎ ለማጎልበት ታሳቢ ተደርጎ የተሾሙ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳደሩ ገልፀዋል።
በዚህም መሰረት አዲስ የተሾሙት የቢሮ ሀላፊዎች፦
1. ዶክተር ኢንጂነር ገብረመስቀል ካህሳይ – የትምህርት ቢሮ ሀላፊ
2. ዶክተር አትንኩት መዝገበ – የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ አንድ ዘርፍ ሀላፊ
3. ዶክተር ተስፋሚካኤል ገብረዩሃንስ – የውሃ ሃብት ቢሮ ሀላፊ
4. ዶክተር አብርሃ ኪሮስ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሀላፊ
5. ዶክተር የትምወርቅ ገብረመስቀል – የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
6. ዶክተር ሙሉጌታ ሀዱሽ – የቴክኒክ እና ሙያ ቢሮ ሀላፊ
የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት፦
1. ዶክተር ፋና ሀጎስ – ፕሬዚዳንት
2. አቶ አማኑኤል አሰፋ – ምክትል ፕሬዚዳንት
ዶክተር ረዳኢ በርኸ ደግሞ የክልሉ የዋና ኦዲተር ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
የቢሮ ለውጥ ያደረጉ አመራሮች፦
1. አቶ ገብረመስቀል ታረቀ – የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
2. አቶ ጎይቶም ይብራህ – የወጣቶች ጉዳይና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ
3. ዶክተር ገብረህይወት ገብረ እግዚአብሄር – የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ