Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢትዮጵያ በወስን ተሻጋሪ ወንዞች ላይ የገነባቻቸው ግድቦች ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትስርርን እየፈጠሩ ነው


አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በወስን ተሻጋሪ ወንዞች ላይ የገነባቻቸው እና እየገነባቻቸው ያሉ የሃይል ማመንጭ ግድቦች ፍትሃዊ የውሃ አጠቀቃምን በማረጋገጥ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትስርርን እየፈጠሩ መሆኑን የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ተናገሩ።

የታለቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት እና የመገናኛ ብዙሃን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየሰሩ ባሉት ስራ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

በውይይቱ ላይ የተገኙት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ መገናኛ ብዙሃን ግድቡን በተመለከተ በተፋሰሱ ሀገራት የተደረሱ ስምምነቶችን በማሳወቅ ረገድ ውጤታማ ስራ መስራቸውን ተናግረዋል።

አብዛኛዎቹ መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛ መረጃን እያደረሱ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ ጥቂት መገናኛ ብዙሃን ግን የተዛባ መረጃን በመንዛት ተጠምደዋል ብለዋል።

በውይይቱ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መከካል እየተደረጉ ያሉ ስምምነቶች ያሉበት ደረጃ እና በወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።