Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

አቶ ጌታሁን ናና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

getahun-nana
አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዲስ ፕሬዚዳንት ሾሙ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዛሬ እንዳስታወቀው አቶ ጌታሁን ናና ባንኩን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

አቶ ጌታሁን ባለፉት ሰባት አመታት የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በአቶ ጌታሁን የተተኩት አቶ ኢሳያስ ባህረ ለስምንት አመታት ልማት ባንክን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወቃል።