Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ችግር ፈጥረዋል በተባሉ ከ640 በላይ የድርጅት አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ


አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) ያደረገውን የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ ተከትሎ ችግር ፈጥረዋል በተባሉ ከ640 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን የድርጅቱ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

በጽህፈት ቤቱ የገጠር ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ ኣቶ አማኑኤል አማረ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በአመራሮቹ ላይ እርምጃ የተወሰደው ህዝብን የሚበድሉ የተለያዩ ችግሮች በመፍጠር ሃላፊነታቸውን በብቃት ባለመወጣት ባሳዩት ድክመት ነው፡፡

በዚህም ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር ተያይዞ የጎላ ችግር አለባቸው የተባሉ 13 አመራሮች በህግ እንዲጠየቁና 22ቱ ደግሞ ከድርጅቱ እንዲባረሩ መደረጉን አመልክተዋል፡፡

ቀሪዎቹ ከከፍተኛ እስከ ጀማሪ ደረጃ ያሉ አመራሮች ደግሞ ከሃላፊነት እንዲነሱና እንዲሸጋሸጉ መደረጉን ጠቁመው በሂስና ግለ ሂስ የታለፉ እንዳሉም ገልጸዋል።

ሃላፊነቱን የሚወጣውንና የማይወጣውን የሚለይ ቀጣይ ግምገማም ወደ ህዝብ የሚወርድ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አማኑኤል፥ በጥፋተኞች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል፡፡

One Response to ችግር ፈጥረዋል በተባሉ ከ640 በላይ የድርጅት አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ