Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ታላቅ የኢትዮጵያውያን ኮንፈረንስ በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ አከባቢ ፌደራሊዝምና የአገራዊ አንድነት ጥያቄ

ታላቅ የኢትዮጵያውያን ኮንፈረንስ
በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ አከባቢ

ፌደራሊዝምና የአገራዊ አንድነት ጥያቄ
የክብር ጥሪ
ተቀራርበን እንዴት የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን አንድነትን ማጠናከር እንደምንችል እንወያይ
ቅዳሜ ፌብርዋሪ 18/2017 [እአአ] ልክ 10.30 A.M በፓትሪክ ሄነሪ ህዝባዊ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት
701 S. Highland St. Arlington, VA, 22204 በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ የታጀበ ታላቅ የኢትዮጵያውያን ኮንፈረንስ ይካሄዳል።
ይህ መድረክ ሁለት ዓላማዎች አሉት
1] የፌደራል መንግስት ስርዓት ከሚከተሉ አገሮች የክልሎቻቸው አንድነትን ለማጠናከርና እንደ አንድ አገር ጠንክረው እንዲቆሙ ለማድረግ የሚከተሏቸው ፖሊሲዎች፣ የመሰረቷቸው ተቋሞች፣ መድረኮች ወዘተ ተሞክሮ ለመቅሰም፣
2] የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን አወንታዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ምን መደረግ እንዳለበት ለመመካከር ነው።
የኮንደረንሱ ተልእኮ የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያ በእኩልነት የተገነባች፣ በዴሞክራሲ የጎለበተች፣ የበለጸገች ጠንካራ አንድነት ያላት አገር እንድትሆንና የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ አንድነት እንዲጠናከር የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ነው። በዚህ ኮንፈረንስ የተለያዩ ክቡራን ሙሁራንና ኤክስፐርቶች የመወያያ ጽሁፍ አዘጋጅተው ተሞክሮ ያካፍሉናል።
ክቡራን የመወያያ ጽሁፍ አቅራቢዎች
ሀ/ ከአሜሪካ
ፕሮፌሰር ጆን ኪንከይድ [ዶ/ር]
በፔንስልቫንያ ስቴት በኢስተን ከተማ ላፍያት ኮሌጅ የሮበርትና ሄለን መይነር የክልሎችና የአከባቢ መንግስታት ጥናት ማእከል ዳይረክተርና በመንግስትና ህዝባዊ አገልግሎት የታወቁ ፕሮፌሰር ናቸው። እኚህ እውቅ የፌደራሊዝም ሙሁር የህዝባዊ መስተዳድር ብሄራዊ አካዳሚ ተመራጭና በአሜሪካን የፖለቲካ ሳይንስ ማህበር የፌደራሊዝምና የመንግስት ለመንግስት ዝምድና ከፍተኛ ተሸላሚ ናቸው። ፕሮፌሰር ጆን በፌደራሊዝም ለሚደረጉ ዓለምአቀፍ ውይይቶች ኤዲተር ሆነው ያገለገሉ ከመሆናቸውም በላይ በፌደረሽኖችና በዓለም አቀፍ የፌደራሊዝም ጥናት ማህበር ማእከል ጥምር ፕሮጀክት ከፍተኛ ኤዲተር በመሆን አገልግለዋል። ከመንግስታት ጋር በሚደረግ ግንኙነቶችም የአሜሪካ አማካሪ ኮምሽን ፈጻሚው አካል ዳይረክተር በመሆን አገልግለዋል። በፌደራሊዝምና በመንግስታት ግንኙነቶችም ብዙ የተለያዩ ሙሁራዊ ጽሁፎች የጻፉ ከፍተኛ የፌደራሊዝም ኤክስፐርት ናቸው።
ለ/ ከቤልጅም
ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ከሚገኝ የቤልጅም ኤምባሲ የሚወከሉ የክብር እንግዳ
ሐ/ ከሕንድ
ወይዘሮ ላክሽሚ ሚታ
ወይዘሮ ላክሽሚ የመጀመርያ የህግ ዲግሪያቸውን ከደልሂ [ሕንድ] ዩኒቨርሲቲ የህግ ማስተርስ ዲግሪያቸው ደግሞ ከዩፒ [ሕንድ] ዩኒቨርሲቲና ሌላ የህግ ማስተርስ ዲግሪ ደግሞ በአሜሪካን አገር በጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ በመከታተል ያሉ ሲሆን በህንድ አገር ጀነራል ኮርፖሬት ኦቶርኒ በመሆን ለአስራ አራት ዓመታት ያገለገሉ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ በደልሂ የሳኬት ባር አሶሲየሽን መስራችና የመላ ሕንድ የባር አሶሲየሽን አባል በመሆን የተለያዩ የመንግስት ጉዳዮችን በመወከልና በማማከር በተለያዩ የህግ መስኮች በከፍተኛ ኤክስፐርትነት ያገለገሉ ባለ ሞያ ናቸው። የሕንድ ኮርፐሬት ሚንስትር ፖሊሲ አርቃቂ ቡድን አባል በመሆንም በግምባር ቀደምትነት ተንቀሳቅሰዋል።
መ/ ከናይጀርያ
ሚስተር አንድሪው ንዱቢሲ ኡችኦሙሙ [ማዚ]
እውቁ የሕግ ጠበቃ ሚስተር አንድሪው ንዱቢሲ ኡችኦሙሙ [ማዚ] በኤኮናሚክስና ፖለቲካል ሳይንስ የቢ ኤስ ዲግሪያቸውን ከፔትስበርግ ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ፣ የጀይ ዲ ዲግሪያቸውን ከዴቪድና ክላርክ የህግ ት/ ቤት ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ አሜሪካ፣ የህግ ማስተርስ ዲግሪ ከአሜሪካ ዩነቨርሲቲ አሜሪካ፣ ከሁል የህግ ት/ቤት ዩናትድ ኪንግዶም ደግሞ ሌላ የህግ የማስተርስ ዲግሪ በሸሪዓ ህግ ያገኙና በዓለም አቀፍ ቢዝነስ የሃያ ዓመታት ልምድ ያላቸው ከፍተኛ የህግ ባለሞያ ናቸው። ሚስተር ማዚ በቴክኖሎጂ ሽግግር በባንግላድሽ፣ በቦሊቭያ፣ በናይጀርያ፣ በእስራኤል ዌስት ባንክና በዚምባብዌ ፋብሪካዎች እንዲገነቡ ያደረጉና በዓለም አቀፍ የብዙ ሚልዮን ዶላሮች ጆይንት ቬንቸር ያስፈጸሙ ከፍተኛ የህግ ባለሞያ ናቸው። ሚስተር ማዚ በወርልድ ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ፣ አፍሪካን ዴቨሎፕመንት ባንክ፣ ኤስያን ዴቨሎፕመንት ባንክ፣ኢንተር አሜሪካን ዴቨሎፕመንት ባንክና በዩ ኤስ ኤግዚም ባንክ የኤኮኖሚ ተቋሞች ባላቸው እውቀትና ሞያ ጎልተው ይታወቃሉ። ሚስተር ማዚ የአሜሪካን ባር አሶሲየሽን፣ ብሄራዊ ባር አሶሲየሽን፣ የሜሪላንድ የሞንት ጎመሪ፣ የፕሪንስ ጆን፣ የፍራንክሊን ቦርንና የፌደራል ባር አሶሲየሽን ኩሩ አባል ናቸው።
የክብር ጥሪ
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያ ክልሎች አንድነት ተደላድሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት እንዲጠናከር በኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራስያዊ ግንባር የሚመራው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊ ሪፖብሊክ [ኢፌዴሪ] መንግስት ተግባር ላይ እያዋላቸው ያሉ ፖሊሲዎች፣ የተቋቋሙ ተቋሞችና አሰራሮችን እንዲሁም እስከ አሁን ድረስ በመስኩ የተመዘገቡ ድሎችና ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ የመወያያ ጽሁፍ እንዲያቀርብልን በክብር እንጋብዛለን።
የሚከተሉት እንግዶች ከታች በተጠቀሱት ርእሶች ዙርያ ያላቸውን እውቀትና ልምድ የሚያካፍለን
የውይይት ጽሁፍ እንዲያቀርቡ በማክበር እንጋብዛለን
ሀ/ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል
[በኢትዮጵያ ወይንም ከኢትዮጵያ ውጭ በፖለቲካ ፓርቲነት በህግ የተመዘገበ] የኢትዮጵያ ፌደራሊዝምና የክልሎችን አንድነት ከማጠናከር አኳያ ያሉ ተጨባጭ ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳብን የሚያመላክት ጽሁፍ
ለ/ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባል
በኢትዮጵያ ፌደራሊዝምና መንግስታት የክልሎች አንድነትን ለማጠናከርና በዝያውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ ባላቸውና ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ዙርያ ጽሁፍ ለማቅረብ በክብር ተጋብዟል።
የኮንፈረንስ ተሳታፊዎች
ሁሉም ጽሁፍ አቅራቢዎች ዝግጅታቸውን ካጠቃለሉ በኋላ የኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ውይይት ይቀጥላል። በዚህ ውይይት [ሀ] የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መሰረታዊ መርሆዎችና ባህርያት፣ [ለ] ከውጭ አገር የፌደራል ስርዓት ተከታዮች የተቀመረው ልምድ የአገራችን ኢትዮጵያ አንድነትን ለማጠናከር እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችልና [ሐ] የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን አንድነትን ለማጠናከር መወሰድ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ውይይት ይደረጋል።
ማሳሰብያ [ለኢትዮጵያውያን የመወያያ ጽሁፍ አቅራቢ እንግዶችና ኮንፈረንስ እንዲሳተፉ ለተጋበዙ በሙሉ
1. መታወቅያ ወረቀትና የመግብያ ትኬት የያዙና የቨርጂንያ ህጎችን የሚያከብሩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የኮንፈረንሱ ተሳታፊ እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል። የመግብያ ትኬቱ ለኮንፈረንስ የተደረጉ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያገለግል $20.00 [ሃያ ዶለር] ነው። ከቦታው ውስንነት አንጻርና ትኬቱ እንዳያልቅ አስቀድመው መግዛት የሚፈልጉ የሚቀጥለው ፎርም ሞልተው በባንክ አካውንት በመክፈል ትኬታቸውን በኢመይል ማግኘት ይችላሉ።
ሙሉ ስም————————————————
ኢመይል አድራሻ ——————————————
ስልክ ቁጥር————————————————
የ ፌደራሊዝም የባንክ አካውንት የሚገኘው በ “Wells Fargo” ሲሆን
Account No. 841 270 1297 Routing No. 051 400 549] ነው።
በአካል ቀርበው ትኬቱን መግዛት የሚፈልጉ ካሽ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ከፖለቲካ ፓርቲና ከዲያስፖራ በኮንፈረንሱ የመወያያ ጽሁፍ እንዲያቀርቡ የተጋበዙ እንግዶች የሚያቀርቡት ጽሁፍ ከሶስት ገጾች የማይበልጥ ማብራርያ አስቀድመው መላክ ይጠበቅባቸዋል።
3. ከፖለቲካ ፓርቲ የመወያያ ጽሁፍ አቅራቢ የሚወክለው ፓርቲ በህግ የተመዘገበ ለመሆኑ የሚያስረዳ መረጃ መላክ ይጠበቅበታል።
4. በተራ ቁጥር 2 እና 3 የተጠቀሱ መረጃዎች የሚላኩት በሚከተለው ኢመይል አድራሻ በፒ ዲ ኤፍ መልክ አታችመንት ሆኖ ለአቶ ሙሉ ሰንደቅ ነው። “[email protected]
5. ከአንድ በላይ የመወያያ ጽሁፍ ከተላከ የመምረጥ ስራ የሚከናወነው ቀድሞ የደረሰ ቅድምያ ያገኛል በሚል መርህ ነው። የፖለቲካ ፓርቲ አቅራቢው ከኢትዮጵያ የሚመጣ ከሆነና መረጃውን ከፌብሪዋሪ 5/2017 በፊት እንዲደርስ ካደረገ ቅድምያ ያገኛል
6. የኮንፈረንሱ አዘጋጅ ለማንኛውም የተሳታፊዎች ወጪ የሚከፍለው ምንም ዓይነት ክፍያ ወይንም ድጎማ አይኖርም።
7. ኮንፈረንሱ ልክ በ10.30 AM ስለሚጀምር የተጋበዙ እንግዶች ልክ በ10.00 AM ቦታቸውን መያዝ ይኖርባቸዋል። ዘግይተው የሚደርሱትን ለመጠበቅ የሚመደብ ግዜ አይኖረንም።
8. ልዩነቶች የእድገት በሮች ናቸው። መቻቻልና የእርስ በርስ መከባበር ደግሞ ዋና መመርያችን መሆን ይኖርባቸዋል። በውይይት ወቅት ስምምነት ያልተደረሰባቸው ልዩነቶች ከተከሰቱ በሰለጠነና በዘመናዊ መንገድ ላለመስማማት መስማማት ይኖርብናል።
የኮንፈረንሱ አዘጋጅ _ አቶ ሙሉ ሰንደቅ

ስለ ኮንፈረንሱ አዘጋጅ

አቶ ሙሉ ሰንደቅ በአሜሪካን አገር ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ናቸው። አቶ ሙሉ የመጀመርያ የክብር የህግ ዲግሪያቸው ከኢትዮጵያ አግኝተዋል። በዚያን ወቅት የኢትዮጵያ አሃዱአዊና ፌዴራላዊ ህገ መንግስታት ታሪክን አጥንተዋል። ከዚያ በኋላ ህንድ አገር በመሄድ የ“ዓለም አቀፍ ህግ”ን አጥንተው በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል። ህንድ አገር በነበሩበት ግዜም የህንድ ፌደራላዊ ህገ መንግስትን አጥንተዋል። በዩ ኤስ አሜሪካ የፉልብራይት ስኮላር በመሆን ደግሞ የአሜሪካ ፌደራላዊ ህገመንግስት አማጣጥና አሁን ያለበት ደረጃን አጥንተዋል። በተጨማሪም አሜሪካ በሚገኘው አሜሪካን ዩነቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን በመከታተል በ“ህግና መንግስት” የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። አቶ ሙሉ እስከ 2003 [እአአ] የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ [ህወሓት] ታጋይ ነበሩ። ክዚያን ግዜ ወዲህ ላለፉት 14 ዓመታት ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር አባል ሳይሆኑ የሚኖሩ ገለልተኛ ናቸው።

ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት ናት። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በማንኛውም የአገሪቱ ክልል የመስራት፣ የመነገድ፣ ሞያውንና አገልግሎቱን የመሸጥና የመኖር መብቶች አሉት።
[የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መግብያ፣ አንቀጾች 32፣ 33፣ 41ና 88]

በመከባበርና በእኩልነት የተገነባች ኢትዮጵያ በደም በአጥንታችን ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች !
ክብር ለኢትዮጵያና በእኩልነት የተገነባ የኢትዮጵያ አንድነትን ለሚወዱ ሁሉ !

Mulu Sendek
December 23/2016
United States of America
[email protected]

4