Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በአዲስ አበባ ሃያ ሺህ ለሚሆኑ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ካሳ ሊከፈል ነው

ታህሳስ 3፣ 2009

በአዲስ አበባ በተያዘው ዓመት ሃያ ሺህ ለሚሆኑ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ካሳ ሊከፈል ነው፡፡
addis-abeba-office
በአዲስ አበባ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ የሚያቋቁም ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በይፋ ስራ ጀመረ፡፡

የመዲናችን አዲስ አበባ እድገትን ለማፋጠን በየአመቱ በርካታ አርሶ አደሮች ተገቢውን የካሳ ክፍያ ሳይሰጣቸው ከይዞታቸው ሲነሱ ይስተዋላል፡፡ ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግስት የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በማቋቋም ተገቢውን የካሳ ክፍያ ለመስጠት እየሰራ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱራዛቅ ያሲን ጽህፈት ቤቱ ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ስራ አርሶ አደሮች በልማት ከይዞታቸው መነሳት ስጋት ሳይሆን የተሻለ ለውጥ እንዲሆናቸው የሚያስችልም ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ በ2009 ዓ.ም. አራት ቅርንጫፎችን በመክፈት 20 ሺህ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም አቅዶ እየሰራ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡