Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በትግራይ ክልል መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ተወሰነ

img_0461
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል መምህራን የመማር ማስተማር ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዲችሉ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ተወሰነ።

የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አታክልት ገብረ ህይወት ውሳኔውን ተግባራዊ ማድረጊያ መመሪያ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

በዚህም በክልሉ የሚገኙ መምህራን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የሚያገኙበት እንዲሁም በተናጠል የመኖሪያ ቤት ለመስራት አቅሙ ላላቸውም በነብስ ወከፍ 140 ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጣቸው እንደሚደረግ ነው አቶ አታክልት የተናገሩት ።

የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘትም እንደየከተሞቹ እድገትና ስፋት መምህራኑ ከ50 ሺህ ብር እስከ 110 ሺህ ብር መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል።
L

በግንባታ ሂደት ላይ ለሚያጋጥማቸው የገንዘብ እጥረትም ከባንክና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዲያገኙ ለማድረግ መታቀዱም ነው የተገለፀው።

የቴክኒክና ሙያ መምህራንም የመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

በትግራይ ክልል በቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ያሉትን ሳይጨምር በአንድኛና ሁለተኛ ደረጃ ከ37 ሺህ በላይ መምህራን እንደሚገኙ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ብሏል ኢዜአ በዘገባው።