Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ያራ ኩባንያ በኢትዮጵያ በማዳበሪያ ማምረት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት አሳይቷል

ህዳር 05፣2009

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአለም አቀፉ ያራ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሬ ሆልሊዘር ጋር ኩባንያው በኢትዮጵያ ሊያከናውናቸው ባሰባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
yara-company
ያራ ኩባንያ በማዕድን ቁፋሮና ማዳበሪያ ማምረት ላይ የተሰማራ ነው፡፡

ኩባንያው በአፋር ክልል የሚገኘውን የፖታሽ ማዕድን በመጠቀም የማዳበሪያ ምርት ለማምረት ፍላጐትም አለው፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሀገሪቱ በምትከተለው ግብርና መር ኢንዱስትሪ የልማት እንቅስቃሴ ላይ ደጋፊ ኢንቨስትመንቶች የግብርናውን ዘርፍ ለማጠናከር ብሎም ዘላቂ ልማትን ለማምጣት እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡