Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በፀረ ሰላም ሃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እንደሚቀጥል ጠ/ሚኃይለማርያም ገለጹ

ጥቅምት 22፡2009
ከህዝቡ ጋር በመተባበር በፅንፈኞች፣ ፀረ ሰላም ሃይሎችና በሽብርተኞች ላይ  የሚወሰደው እርምጃ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡
parlama-meeting-on-10312016
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት መስከረም 30 ለህዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግርን አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በውስጥ የአገራችን ጉዳዮች የግብፅ ጣልቃገብነትን አስምልክቶ መንግስት ለግብፅ መንግስት ግልፅ ጥያቄ አቅርቦ በጣልቃ ገብነት የተጠቀሱት ተቋማት ከግብፅ መንግስት ቁጥጥት ውጭ ያሉ መሆናቸውን በመግለፅ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ እንደተሰጠው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡ 
የግብፅ መንግስት በአገራቸው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቋማትን እንዲቆጣጠር የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚቀጥልና ኢትዮጵያም የሰከነና ሃላፊነት የተሞላበት ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ፡፡
በውጭ አገራት የሚኖሩ ፅንፈኛ የዲያስፖራ አካላትም ኢትዮጵያን ለመበታተን ያላቸውን ሴራ በግልፅ ሳያፍሩ በማንፀባረቅ ላይ መሆናቸውንና በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት መጋለጣቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ የፅንፈኛ ሃይሎቹ መጥፊያ ቅርብ ነው ብለዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስመልክቶ ለተነሳው ጥያቄም አዋጁ የአገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡ አዋጁ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ጀምሮ በየቦታው በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት ይጠፋ የነበረውን የሰው ህይወት ለመታደግ ተችሏልም ብለዋል፡፡
በኮማንድ ፖስቱ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማስፈፀሚያ ደንብም እንደያስፈላጊነቱ በየጊዜው የሚሻሻል ሲሆን እንደምሳሌም የዲፕሎማቶችን መዘዋወር የሚገድበው መመሪያ በአሁኑ ወቅት ለቱሪስቶችም ሆነ ለዲፕሎማቶች በመላው አገሪቱ የሚያሰጋ ጉዳይ ባለመኖሩ በቅርቡ ሊነሳ እንደሚችል ጠቅላይ ሚንስት ኃይለማሪያም ጠቁመዋል፡፡
የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ጉዳይን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄም ለጉዳዩ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጠውና ችግሩን ለመቅረፍ ፈንድ ከማቋቋም ባለፈ ወጣቶችን የፓኬጁ ባለቤት በማድረግ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የመልካም አስተዳደር ጉዳይንም አስምልክቶ ለተነሳው ጥያቄ ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ እስከ ታችኛው የህብረተሰብ አገልጋይ ሰራተኛ ድረስ ለውጥ ለማምጣት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ህብረተሰባዊ ተሃድሶ ሊያመጣ የሚያስችል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን እንደ መልካም አስተዳደር ጥያቄ አድርጎ ማቅረብ ከአገሪቷ አቅም አንፃር ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሊመራ እንደሚችልም ጠቅላይ ሚንስትሩ አብራርተዋል፡፡
በተፈለገው ደረጃ ላይ ያልደረሰው የሚድያ ዘርፍ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችም በተለይ በአዲሱ ካቢኔ አወቃቀር በእውቀት ላይ በተመሰረተ ባለሞያ እንዲመራ ከማድረግ ባሻገር በዘርፉ ያሉ ባለሞያዎችን እውቀትና ክህሎት ለማሻሻል በዩኒቨርስቲዎችና በከፍተኛ የትምርት ተቋማት ደረጃ ትኩረት እንደተሰጠው ተገልጿል፡፡
ሞሽኑም ውሳኔ ቁጥር 2/2009 ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡