Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በኢትዮጵያ መንግስት እና በኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ

ጥቅምት 24፣2009
በኢትዮጵያ መንግስት እና በኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ።
ethiopian-arbegnoch
የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር የኢፌዲሪን ሕገመንግስት በመጻረር የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርጎ ሲታገል ቆይቷል።
 ግንባሩ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ከመንግስት ጋር የተለያዩ ውይይቶችን አድርጎ የትጥቅ ትግል አማራጩን በመተው በሰላማዊ መንገድ ለመታገልና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በመቀበል ለመንቀሳቀስ እና ለኢትዮጵያ ሔራዊ ጥቅም ለመቆም መወሰኑን ገልጿል።
ስምንት ነጥቦች ያሉት የሰላም ስምምነትም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተፈራርሟል።
የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በትጥቅ ትግል ውስጥ የነበሩ የተለያዩ ድርጅቶችና ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ እየገቡ መሆናቸውን ገልጸው የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባርም የዚሁ አካል ነው ብለዋል።
 መንግስት የትጥቅ ትግል አማራጭን በመተው በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ የሚፈልጉ አካላትን ለመቀበል ሁሌም ዝግጁ መሆኑንም የመከላከያ ሚንስትሩ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር ሊቀመንበር አቶ ቱዋት ፖል ቻይ ከጦርነት ምንም የሚገኝ ነገር ስለሌለ ወደ ሰላማዊ አማራጭ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ለሰላማዊ ትግል የተመቸ በመሆኑ አባሎቻቸውን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገሉም ገልጸዋል።