Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባቀረቡት የካቢኒ አዳዲስ እጩ አባላት ላይ እየተወያየ ነው

new-cabenit
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የካቢኒያቸውን አዳዲስ እጩ አባላት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ቀደም ሲል የነበረው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ በክላስተር የማስፈፀም  እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሚሉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ መቅረታቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሉበት ይቀጥላሉ ያሏቸው የካቢኒ አባላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን  ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ናቸው።
አዲስ የቀረቡት እጩ የካቢኒ አባላትም፦
1. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
2. አቶ ታገሰ ጫፎ፦ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር 
3. ዶክተር አብረሃም ተከስተ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር 
4. ዶክተር በቀለ ጉላዶ፦ የንግድ ሚኒስትር 
5. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፦ የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር 
6. ዶክተር ኢያሱ አብረሃ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር 
7. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 
8. አቶ አህመድ ሺዴ፦ የትራንስፖርት ሚኒስትር 
9. ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር 
10. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፦  የኮንስትራክሽን ሚኒስትር 
11. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦ የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር
12. አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር 
13. ዶክተር ገመዶ ዳሌ፦ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
14. ዶክተራው ሽፈራው ተክለማርያም፦ የትምህርት ሚኒስትር
15. ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ፦ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር  
16. ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር 
17. ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም፦  የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
18. ዶክተር ደሚቱ ሃምቢሳ፦  የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ርስቱ ይርዳው፦ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር 
20. አቶ ከበደ ጫኔ፦ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚኒስትር
21. ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፦  የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ናቸው።