Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ22 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

img_0315
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት በምስራቅ አፍሪካ በአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) ሳቢያ የተከሰተውን ድረቅ ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ 66 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ሊያደርግ ነው።

ድጋፉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሶማሊያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የሚውል መሆኑም ታውቋል።

ህብረቱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከአጠቃላዩ ድጋፍ ለኢትዮጵያ 22 ነጥብ 5፣ ለሶማሊያ 8፣ ለሱዳን 8 እንዲሁም ለደቡብ ሱዳን 28 ሚሊየን ዩሮ ይደርሳቸዋል።

የህብረቱ ዓለም አቀፍ ትብብርና ልማት ኮሚሽነር ኒቪን ሚሚካ ድጋፉ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በአጭርና በረዥም ጊዜ እንዲረዱ ለማድረግ ነው ብለዋል።

የሚደረገው ድጋፍ ለሰብዓዊ እርዳታ፣መልሶ ለማቋቋምና እንዲያለሙ ለማድረግ አስተዋጾ እንደሚኖረውም ገልጸዋል።

ከድርቅና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች በቀጠናው በርካቶች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።

የአውሮፓ ህብረት አህጉራዊ ልማትን ለመደገፍና በሰሜንና በአፍሪካ ቀንድ አገራት ስደትን ለመከላከል ከ75 ሚሊዮን ዩሮ በላይ በመመደብ የልማት ፕሮጀክቶችን እየደገፈ እንደሆነ ይታወቃል።

በተለይ ከሁለት ዓመት በፊት ለግብርና፣ለምግብ፣ለጤና፣ለኃይል አቅርቦት፣ለመንገድና ለሌሎች መሰረተ ልማት ዘርፎች የሚውልና እስክ አውሮፓውያኑ 2020 የሚቆይ የ745 ሚሊዮን ዩሮ ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጹ ይታወሳል።