Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደትን የሚቃኝ ሀገር አቀፍ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ

scholars-meeting-in-addis
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደትን የሚቃኝ ሀገር አቀፍ ውይይት በሽራተን አዲስ ተካሂዷል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከተለያዩ ባለድረሻ አካላት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ “የሀገራችን የዴሞክራሲና የፌዴራል ስርዓት ከየት ወደ የት” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ አገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የማያቋርጥ ሂደት መሆኑን አንስተዋል።
አሁን ላይ ባለው ሂደትም መሟላትና መመለስ የሚገባቸው የዴሞክራሲ ጥያቄዎች እንዳሉ ነው የተናሩት።
ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ሂደት በተለይም የአገሪቱን የምርጫ ህግ በማሻሻሉ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሚደረግ ድርድር የሚፈጸም ነው ብለዋል።
aba-dula
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዱ ይመስል በበኩላቸው የህዝቡን የልማት እና የዴሞክራሲ ጥያቄ በማስቀደም የአገሪቱን ዴሞክራሲ ባህል ማዳበር እንደሚገባ ነው ያመለከቱት።
ይህም መድረክ ሲዘጋጅ የአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በፍፁም ቅንነት የሀሳብ ትግል በማድረግ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ በማሰብ ነው ብለዋል።

shcolars-1
በውይይቱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክና የሙያ ማህበራት፣ የግል ባለሃብቶች፣ ምሁራን እንዲሁም የመንግስት ስራ አሰፈፃሚ አካላትን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እየተሳተፉ ይገኙበታል።
በውይይት መድረኩ ላይ የዴሞክራሲና የፌዴራል ስርዓት ሂደቱን የሚቃኙ አራት ጽሁፎችም በተሳታፊዎች ቀርበዋል።

scholars-2
በውይይት መድረኩ ላይ አራት ጽሁፎች አራት ጽሁፎች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል።
የመጀመርያው ጽሁፍ አቅራቢ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖሊቲካል ሳይንስ መምህር ዶክተር ካሳሁን ብርሀኑ ሲሆኑ፥ በጽሁፋቸው ከ1966 ዓ.ም የከሸፈ ካሉት አብዮት ጀምሮ እከካሁን ድረስ ያለውን የፌዴራል ዴሞክራሲ ግንባታን ዳሰዋል።
የአሁኑ መንግሰት ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ አንጻራዊ ሰላም መጥቷል፤ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታም መንገድ ተከፍቷል ያሉ ሲሆን፥ ህገ መንግስቱ ለብሄሮች እንጂ ለሀገር ስሜት ብዙም ቦታ አልሰጠም ከሚሉ ስጋቶች ውጭ ብዙ ይዘቶቹ ተቀባይነትን ያገኙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ሆኖም አሁን ላይ ያለ የመልካም አተተዳደር ችግር እጅግ ሰፊ መሆኑን ይሀም በመንግስት የታመነ ተግዳሮት ነው ብለዋል።
መንግስት ለግልም ሆነ ለቡድን ጥቅም የመንበርከክ አዝማሚያ፣ በመንግስት ተቋማት ላይ የቁጥጥር ማነስ፣ በመንግስትና ፓርቲ መካከል ልዩነት እየጠፋ መምጣቱም የሚታዩ ችግሮች መሆናቸው በዶክተር ካሳሁን ጽሁፍ ቀርቧል።
የዴሞክራሲ ተቋማት የመንግስት መሆናቸው እንዲሁም አንዳንድ ህጎች መውጣታቸው ችግር ባይኖረውም አፈጻጸማቸው ግን ችግር ያለበት ነው ሲሉ በጽሁፋቸው አቅርበዋል።
ከባለሀብቶች በኩል ጽሁፍ ያቀረቡት የፍሊንት ስቶን ሆምስ ባለቤት ኢንጂነር ጸደቀ ይሁኔ ሲሆኑ፥ የፌዴራል ስርአቱ ከተመሰረተ 25 ዓመት በኋላ ዛሬ ላይ አጓጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ለግልም ሆነ ለቡድን መብት የተመቻቸ ስርአት መኖሩና ጭቆናን መሸከም የማይችል ሞጋች ህብረተሰብ መፈጠሩ ናቸው ብለዋል።
የሰርአቱ ቀዳሚ ተጠቃሚዎች አድሎአዊ በሆነ ጥገኝነት መዘፈቃቸው እንዲሁም ያለመቻቻልና ያለመነገገር ለብሄራዊ መግባባት እንቅፋት መሆናቸውን በአስጊ ሁኔታ ጠቅሰዋል።
ኢንጂነር ጸደቀ አሁን በሀገሪቱ የተለያዩ ችግሮች መፈጠር በፖሊቲካው ሆነ በኢኮኖሚ ላይ የነበሩ ምክንያቶችን ጠቅሰው፤ ኢህአዴግ በጥልቀት መታደስ ሳይሆን እንደገና መፈጠር ነው ያለበት ብለዋል።
ከተቃዋሚ ፓርቲ በኩል ጽሁፍ ያቀረቡት ደግሞ አቶ አቶ ልደቱ አያሌው ናቸው።
አቶ ልደቱ፥ በሽግግሩ ጊዜ የነበሩ ነገሮችን ዘግይቼ ነው የተቀበልኳቸው፤ አሁን ያለንበት ሁኔታ ከዚያ ጊዜ ያነሰ ነው በሚል ይዘት ጽሁፋቸውን ጀምረዋል።
በሽግግሩ ጊዜ የመድብለ ፓርቲ ከአሁን የተሻለ ገጽታ ነበር፤ በርካታ ጋዜጦች ይታተሙ ነበር ፤ በምክር ቤቶችም ተቃዋሚችች ነበሩ ብለዋል።
አሁን ያለው ግን በዚህ በተቃራኒ ሆኗል፤ አሁን በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የታዩ ችግሮች ያኔ ኢህአዴግ ከህዝቡ ፍላጎት ውጭ ፓርቲ መስርቶ ማደል ሲጀምር ነው የጀመሩትም ነው ያሉት ።
የመገናኛ ብዙሀን መታፈን፣ ሚዲያ ማህበራት በቁጥጥር ስር መዋል እንዲሁም በህገመንግስቱ የብሄሮች መብት ቦታ ማግኘቱ ችግር ባይኖረውም ኢትዮጵያዊነት ቦታ አጥቷል ብለዋል።
ኢህአዴግ ከ2002 ምርጫ ተምሮ 2007 ተቃዋሚዎች መቀጨጫ እንዲናራቸው ያደርጋል ብለን ብንገምትም የነበረው አንድ ወንበርም ቀርቷል ብለዋል አቶ ልደቱ።
ይህ ህዝቡ የሚተነፍስበትን አሳጥቶ ጎዳና አስወጥቶታል፤ ምክንያታዊነት ቦታ ማጣቱም ለጽንፈኝነት መንገድ ከፍቷል፤ እስከ አቸቸኳይ ጊዜ አዋጅ የነነነነውም በዚህ ነው ሉሉ ጠቅሰዋል ።
ውስጣዊ ዴሞክራሲ መኖር፣ ሽብርኝነትን መከላል መቻሉን እና በሁሉም መስክ የተመዘገው ልማት የኢህአዴግ ጥንካሬ ነው ብለዋል።
በመጨረሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በኢህአዴግ በኩል የመጡት አቶ በረከት ስምኦን ናቸው።
ኢህአዴግ ከ15 የተሀድሶ አመት በሁኋላ በሀገሪቱ የተፈጠሩ ችግሮች ማብራሪያ የሰጡት አቶ በረከት፥ ግጭቶቹ ሀገሪቱን የማፍረስ አቅም አላቸው ብዬ አላምንም ብለዋል።
በአንዳንድ ስፍራዎች ግጭቶች የተከሰቱትም ጠያቂ ህብረተሰብ በመፍጠራችን የመጣ ነው ብለዋል።
ህዝቡ በፌዴራሊዝም ስርአቱ ላይ ችግር የለበትም ሲሉም አቶ በረከት በጽሁፋቸው አብራርተዋል።
ያለፉት ሁለት መርጫችች በኢህአዴግ ሙሉ የበላይነት መጠናቁቁ ኢህአዴግ ራሱም አምኖ የምርጫ ስርአቱን ለማስተካልል እየሰራ ነውም ብለዋል።
ጽሁፎቹ በዚህ መልኩ ተጠናቀው የተለያዩ ውይይቶች በመድረኩ ላይ ተካሂደዋል።
በውይይቱ ላይ ከ250 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።