አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ኢ ቲ ኤ ኤን ዋይ የተባለ ቦምባርዲየር ኪው400 የአገር ውስጥ የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 212 የመንገደኞች አውሮፕላን በዛሬው እለት ጥር 14 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር በማኮብኮብ ላይ እያለ የዱር እንሰሳት በማኮብኮቢያው ላይ በመግባታቸው በረራው ተቋረጠ።
ዓየር መንገዱ ማምሻውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ 74 መንገደኞች እና ስድስት የበረራ ሰራተኞች በሰላም ወርደዋል።
ዓየር መንገዱ በዚህ አጋጣሚ መንገደኞች ለደረሰባቸው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።
እንዲሁም የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ላሳዩት የሙያ ብቃት ዓየር መንገዱ አድናቆቱን ግልጿል።