Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ፖሊስ በአዲስ አበባ ፀረ ሰላም ሀይሎች ከሚያናፍሱት ወሬ ውጪ ሁሉም እንቅስቃሴ ሰላማዊ ነው አለ ፖሊስ

federal-police
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) “በአዲስ አበባ ፀረ ሰላም ሀይሎች ከሚያናፍሱት ወሬ ውጪ ከተማዋ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ትገኛለች” ሲል ፖሊስ ገለፀ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ጀነራል አሰፋ አብዩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዜና መፅሄት እንደተናገሩት፥ በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ውስን ቦታዎች ላይ ትናንት እና ዛሬ በኢሬቻ በዓል ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ ሁከት ለማስፋፋት ጥረት ተደርጓል።
በዚህ ሙከራም ከውጭ ሀይሎች ትእዛዝ በመቀበል ለሁከት የሚሰሩ እና የሚፈጠሩ ግርግሮችን በመጠቀም በተለይም ፋብሪካዎች አከባቢ ለዘረፋ የተቀላቀሉ ሰዎች መሳተፋቸውን ነው ያመለከቱት።
በሂደቱ ውስጥ ያለምንም መረጃ እንዲሁ የተቀላቀሉ እንዳሉም ተናግረዋል።
ነገር ግን በእነዚህ ቦታዎች የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን ህገወጥ እንቅስቃሴውን መቆጣጠር መቻሉን ነው ዋና ጀነራል አሰፋ አብዩ የተናገሩት።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከአዲስ አበባም ሆነ በዙሪያዋ የሚገኙ ከተሞች ከሚገኙበት ነባራዊ ሁኔታ የራቀ የበሬ ወለደ ወሬ መነዛቱን አንስተዋል።
ይህም የመዲናዋ ነዋሪ በዓመፅና ሁከት ተግባር እንዲሳተፍ የተሰራጨ መሆኑን ህብረተሰቡ ተረድቶ መደበኛ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የፀጥታ ሀይሉም ከህዝቡ ጋር በመሆን ለየትኛውም የአመፅና ሁከት ተግባር ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ያስታወቁት።