Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ጨፌው አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

chwfew
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ ሁለተኛ አመት መደበኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
በዛሬው መርሀ ግብር በሀገሪቱ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል። 
የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ሀገሪቱ ተጋርጦባት በነበረው የሁከት ስጋት ምክንያት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ቀድሞው ሰላምና መረጋጋት እንድትመለስ እያገዛት ነው ብለዋል። 
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለጨፌው ገለፃ ባደረጉበት ወቅት አዋጁ ሰላም ወዳዱን ህብረተሰብ እና ሀገሪቱን ለመጠበቅ ታስቦ የወጣ እንጅ ህዝብ ላይ ስጋት እንዲፈጠር የወጣ አይደለም ብለዋል። 
ይህንንም ጨፌው ተረድቶ ለተወከለበት አካባቢ የማስረዳት እና ለትግበራው የበኩሉን የመወጣት ሀላፊነት አለበት ነው ያሉት። 
ከጨፌው አባላት የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፥ የአዋጁ ትግበራና የኮማንድ ፖስቱ የስራ አፈፃፀም በምን ይዘት ላይ እንደሚገኝ ከአባላቱ ተጠይቋል። 
በሌላ በኩል አዋጁን የተመለከቱ መረጃዎችን ለህዝቡ በአግባቡ ማድረስ ላይ እና የሰብአዊ መብት አጠባበቅ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የጨፌው አባላት አንስተዋል። 
በተነሱት ጥያቄዎች ላይ አፈ ጉባኤው አቶ አባዱላ ገመዳ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ኮማንድ ፖስቱ ተቀናጅቶ እየሰራ ባለው ስራ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችሏል ብለዋል። 
ውይይቱ ነገም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን የተለያዩ ሹመቶች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።