Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ግድቡ ከሃይድሮ ፓወር ሳይንስ አንፃር ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጥቅሙ ላቅ ያለ ሆኖ ሳለ ግብፅ ለምን የተሳሳተ መንገድን መረጠች?

hydropower
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጥናት አረጋግጣ ወደ ግንባታ የገባችው ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ አጋምሳለች።

ሀገሪቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጥርጣሬ ለመፋቅ አለም አቀፍ ባለሙያዎች በግድቡ ላይ ጥናት አካሂደው ምክረ ሀሳብ እንዲለግሱ እስከ ማድረግ ዘልቃለች።

ሱዳን ግድቡ እንደሚጠቅማት አረጋግጣ የግድቡን ግንባታ እንደምትደግፍ ብትገለፅም ግብፅ የግድቡን ግንባታ የማስተጓጎል አላማ ያላቸው ድርጊቶችን ሰትፍፀም ተስተውሏል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የምህንድስና ምሁር ከሃይድሮ ፓወር ሳይንስ አንፃር ታላቁ የህዳሴ ግደብ ታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ስለመጥቀሙ ጥርጥር የለውም ይላሉ።

እውነታው ይህ ከሆነ ግብፅ ለምን የተሳሳተ መንገድን መረጠች?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና መምህሩ እና የኤም ኤች ኢንጅነሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር መሰለ ሃይሌ፥
ከሃይድሮ ፓወር ሳይንስ አንፃር ሲታይ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እና የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የጥቅም ትሰስር እንዲህ ነው ይላሉ።

ሱዳን የአባይ ውሃን ተጠቅማ መረዌ ከሚባል ግድብ የኤሌክትሪክ ሃይል ታገኛለች።

ግብፅ መስኖዋን አጠጥታ፤ የዜጎቿን ጉረሮ አርሳ፤ በአባይ ውሃ ከአስዋን ግድብ የኤሌክትሪክ ሀይል ታገኛለች።

የአባይ ውሃ በክረምት ወቅት ይህንን ሁሉ ተግባር ከውኖ የተረፈው የሜዲትራንያን ባህርን ይቀላቀላል።

አስዋን በብዙ ቢሊየን ኪዩቢክ ሊትር የሚለካ ውሃን በትነት ያጣል፤ የአባይ ውሃ ከኢትዮጵያ ጠራርጎ በሚወስደው አፈር
አሳዋን እና የመረዌ ግድብን በደለል ሞልቶ ከተሞቻቸውን በጎርፍ ያጠለቀልቃል።

እናም ታለቁ የህዳሴ ግድብ ሀገራቱን ከዚህ ችግር የሚታደግ መሆኑን ነው ምሁሩ የተናገሩት።

ግድቡ ተቆጥሮ የማያልቅ ጥቅምን ለሶስቱም ሀገራት እንደሚሰጥ በሳይንስ የተረጋገጠ ሃቅ ነው።

ሶስቱ ሀገራትም ይህንን እውነት ያጡታል ተብሎ አይጠበቅም።

ስለዚህ በታላቁ የህዳሴ ግደብ ላይ በትንሹ ሊነሳ የሚችለው ጉዳይ የውሃ መሙያ ጊዜው ነው።

ዶክተር መሰለ ይህም በሳይንስ ደረጃ ከታየ በቀላሉ በድርድር ሊፈታ የሚችል ጉዳይ ነው የሚል ሃሳብ ያነሳሉ።

እናም ከሃይድሮ ፓወር አንፃር ታላቁ የህዳሴ ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ለትብብር የሚጋብዝ የጋራ ፕሮጀክት መሆን ነበረበት።

ሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትም ኢትዮጵያ በግዙፍ ፕሮጀክቷ እየመጣች ላለው ትሩፋት ብድራትን በከፈሏትም ነበር ይላሉ ምሁሩ።

ሱዳን ይህንን እውነት ስላወቀች፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን እንደምትደግፍ ይፋ ካደረገች ሁለት አመታት ተቆጥረዋል።

ግብፅ ግን ብዙ የስምምነት መንገዶችን አሳብራ ከመጣች በኋላ ለረጅም አመታት ውስጥ ለውስጥ ስትጎነጉን የነበረውን
የግድቡን ግንባታ የማስተጓጎል ሀሳብ የሚያጋልጡ ተግባራትን እየፈፀመች ትገኛለች።

የውሃ ሳይንሱ ታላቁ የህዳሴ ግደብ ከግድቡ ባለቤት ኢትዮጵያውያን እኩል ግብፅ እና ሱዳናውያን እንደሚጠቅም ካረጋገጠ፤ ግብፅ ከሳይንሳዊ ውጤቱ በተቃራኒ ለመጓዝ የተሳሳተ ቁማርን ለመቆመር የመረጣቸው ለምንድን ነው?

አቶ መለሰ “ሀይድሮ ፓወር ላይ የሚያጣላ ነገር የለም፤ ምክንያቱም ውሃ አይያዝም፤ ነገር ግን የግብፅ ሀሳብ ኢትዮጵያ ስታድግ ኋላ ላይ ጥያቄ ታነሳለች፤ ስለዚህ እዚያው ላይ እንያዛት፤ ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜ እንከልክላት የሚል ነው” ብለዋል።