Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ግሎባል ግሪን ግረውዝ ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ድጋፍ አደርጋለሁ አለ

global-green-growth-instutute
ጥቅምት 07፣ 2009
የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ለማስቀጠል ድጋፍ እንደሚደረግ የግሎባል ግሪን ግረውዝ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍራንክ ሪጅስበርማን ገለፁ።
ኢንስቲትዩቱ ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙያዊ እገዛና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንም ጠቅሰዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይ ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከኢፌዲሪ የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ጋር መክረዋል።
ዳይሬክተሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዓለም አቀፍ ተቋማት ለአረንጋዴ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ለየአገራቱ በየዓመቱ 100 ቢሊዮን ዶላር በላይ ፈንድ ያደርጋሉ።
ይሁንና እነዚህ አገራት ገንዘቡን በሚፈለገው ጊዜ ባለማግኘታቸው የአየር ንብረት ችግር ለመቋቋም የሚቀረፁ ፕሮጀክቶች ተፈፃሚ ሳይሆኑ ይቀራሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚን በመተግበርና የአየር ንብረት ተፅእኖን በመቋቋም ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
በቀጣይም ትብብሩን በማጠናከር እንዲሁም ፕሮጀክቶች ተፈፃሚ እንዲሆኑ ፈንድ በማፈላለግ ድጋፍ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው ከኢንስቲትዩቱ ጋር በካይ ጋዞችን በመለካትና በመመዝገብ፣የልምድ ልውውጥ እንድጠናከርና ተቋማዊ አቅም በመፍጠር ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ለዚሁ ስራ ማስፈፀሚያ ከአንድ ሚሊዮን ደላር በላይ ኢንስቲትዩቱ መድቦ እንደሚንቀሳቀስና ባለሙያዎችንም እንደሚያሰማሩ ነው ያስረዱት።
ግሎባል ግሪን ግረውዝ ኢንስቲትዩት እ.አ.አ በ2010 በደቡብ ኮሪያ የተቋቋመ ሲሆን 26 አባል አገራት አሉት።
ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮም 16 አገራት የአረንጋዴ ልማት ዕቅድ እንድነድፉ በጥናትና ምርምር እና ሌሎች ድጋፎች ሲያግዝ ቆይቷል። በመስራት ይታወቃል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ብራዚል፣ካምቦዲያ፣ቻይና፣ህንድ፣ኢንዶኖዥያና ደቡብ አፍሪካ ከአገራቱ መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ኢዜአ  ዘግቧል።