Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የጨፌው አባላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሁከትና አለመረጋጋት የነበረባቸው አከባቢዎችን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለሱን ገለፁ

chefe-oromia
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው ሁከትና ግርግር ያስከተለውን ጉዳት እና ህዝቡ ላይ የፈጠረውን ስጋት ተከትሎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሁን ላይ ሁከቱ ተፈጥሮባቸው በነበሩ አካባቢዎች መረጋጋትን እያሰፈነ መሆኑን የጨፌ ኦሮሚያ አባላት ገለፁ።

ከፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው የጨፌው አባላት በአከባቢያቸው ባለፉት ጥቂት ወራት በሁከቱ ምክንያት ስጋት ተፈጥሮ እንደነበር አንስተዋል።

ሁከቱ ከፈጠረው ስጋት በተጨማሪ የህዝብና የመንግስት ንብረቶችን ጨምሮ የጋራ መገልገያ ተቋማት ላይም ጉዳቶች ሲደርሱ እንደነበር ነው ያስታወሱት።

ይሁን እንጂ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከወጣና ወደ ተግባር ከተገባ በኋላ ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ከሐረርጌ፣ ወለጋ፣ ጉጂና ሰበታ አካባቢዎች ተወክለው የመጡ የጨፌው አባላት ሲፈጠሩ የነበሩት ሁከቶች እና ንብረት የማውደም ተግባር ሙሉ በሙሉ መቆሙን ነው የገለጹት።

በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰላምና መረጋጋት እንዲመለስ አስችሎ የወከላቸው ነዋሪ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴው ተመልሷል ብለዋል።

የጨፌው ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር በበኩላቸው በእስካሁኑ ሂደት አዋጁ በክልሉ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ስራው በኮማንድ ፖስት የሚመራ ቢሆንም የህዝቡና የጨፌው አባላት ትብብር ሲታከል የታለመለትን ዓላማ በሚገባ ማሳካት ይቻላልም ነው ያሉት።