Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል

ethio-djoubti
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል።
የባቡር መስመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌህ በለቡ ባቡር ጣቢያ ተገኝተው ይመርቁታል።
በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ፕሮጀክት የኮሙዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የፕሮጀክቱን ምርቃት ተከትሎም ወደ ሙከራ ስራ የሚገባ ነው የሚሆነው።
የሙከራ ስራውም በአማካይ ከ3 እስከ 5 ወራት የሚፈጅ ሲሆን፥ ሙከራው ሲጠናቀቅም አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን ገልፀዋል።
3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር መስመር፥ የእቃ ማጓጓዣና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ነው። 75 ፉርጎ ባላቸው ባቡሮች አማካኝነትም እቃዎችን ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሃገር ውስጥ ያጓጉዛል።
ፉርጎዎቹ እስከ 400 ኩንታል የመጫን አቅም ያላቸው ሲሆን፥ በአንድ ጉዞም 3 ሺህ ቶን ጭነትን ማመላለስ ይችላሉ።
ከጂቡቲ ወደብ ወደ መሃል ሃገር የሚደረገው ጉዞም በ10 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ከዚህ ባለፈም እስከ 2 ሺህ 400 ተሳፋሪዎችን የሚይዙና 30 ፉርጎ ያላቸው ባቡሮችም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣሉ።
እነዚህ ባቡሮች ምቹ መኝታ ያለው ልዩ ክፍል እና ዘመናዊ የማብሰያ ክፍሎች እና ካፍቴሪያዎችንም ይዘዋል።
የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መስመር ስራ ሲጀምር ለ5 ሺህ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ይፈጥራል።