Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የኢትዮጵያ መንግስት ለ140 የኤርትራ ስደተኛ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ሰጠ

eritrean-given-scolars
በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ከትናንት በስቲያ ሽኝት የተደረገላቸው ስደተኛ ተማሪዎቹ ለመማር ምቹ ሁኔታ የፈጠረላቸው የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም ማህበረሰብ ዘንድ ምስጋና ሊቸረው እንደሚገባ ገልጸዋል።
የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳዮች አስተዳደር የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስተባባሪ አቶ ተኪኤ ገብረየሱስ በሽኝት ስነ-ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት፣ የትምህርት ዕድሉ ከተሰጣቸው አጠቃላይ ስደተኛ ተማሪዎች መካከል 80ዎቹ በዞኑ በሚገኙ አራት የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያዎች የነበሩ ናቸው።
ቀሪዎቹ 60 ስደተኛ ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ የመጡ ሲሆኑ፣ የትምህርት ዕድል ከተሰጣቸው ተማሪዎች ውስጥ ሰባቱ ሴት መሆናቸውን አስተባባሪው አስረድተዋል።
አቶ ተኪኤ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት ለስደተኞች ከትምህርት ዕድል በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እንደማንኛውም ዜጋ ሰርተው እንዲኖሩና ሌሎች መሰል እድሎችን በማመቻቸት ላይ ነው።
የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚ ከሆኑ ስደተኛ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ዮናስ አሸብር በኤርትራ እያለ የትምህርት ጥማት የነበረው ቢሆንም  እስካሁን ድረስ የመማር ዕድል ሳያገኝ መቆየቱን ተናግሯል።
የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራዊያን ስደተኞችን ለማገዝ እያደረገው ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የቀጣይ ግንኙነት መሰረት ሊሆን እንደሚችል ያለውን እምነት ገልጿል።
የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ተወካይ ሚስ ሶፊ ሎጎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ስደተኞችን ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ስደተኞቹን ከመቀበል ባለፈ ከዜጎቹ ጋር መማር እንዲችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን ተወካዩ አድንቀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ለአንድ ሺህ 500 ኤርትራውያን ስደተኞች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ማድረጉን አስተዳደሩን ጠቅሶ የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው።