Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

tigray-council
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት 5ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በመቀሌ ከተማ ማካሄድ ጅምሯል።

የምክር ቤቱ አባላት በ2009 በጀት ዓመት በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን አስመልክቶ በወጣው እቅድ ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

በእቅዱ በተያዘው ዓመት በክልሉ የመልካም አስተዳደርን በማስፋን ከከፍተኛ አመራር ጅምሮ እስከ ታችኛው መዋቅር በመታደስ የአመራር ሽግሽግ እንደሚካሄድ ተጠቅሷል።

ለምክር ቤቱ የቀረበው የ2009 እቅድ በክልሉ መልካም አስተዳደር ለማስፈን እና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስገኘታቸውን በመነሻነት አስቀምጧል።

ይህም አሁን ለተያዘው በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ትልቅ ግብዓት በመሆን ይጠቅማልም ይላል።

በዚህም አመራሩን የማጥራት ስራ እስከታችኛው ድረስ መዋቅር ድረስ እንደሚቀጥልና በመልካም አስተዳደር ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ተለይተው በታቀደው መልኩ ለማስፈፀም ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ በእቅዱ ላይ ተመልክቷል።

በገጠር የመስኖ እና የእንስሳት ሃብት ልማትን በማሳደግና የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ይሰራል ተብሏል።

በከተሞችም በጥቃቅንና አነሰተኛ ኢንተርፕራይዞች ወጣቶች በተለያዩ መስኮች እንዲደራጁ በማድረግ በከተሞች ያለን የስራ አጥነት ቁጥር ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቷል።

በተያዘው የበጀት ዓመት በክልሉ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ሲሆን ፥ በተያዘው በጀት ዓመት 11 ነጥብ 5 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብም ነው የታቀደው።

ለኢንዱስትሪ እና ለአገልግሎት ዘርፎችም የድርሻቸውን እንዲወጡ ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል።

የምክር ቤቱ አባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ውይይት ሲደረግበት ቆይቷል።

የምክር ቤቱ አባላት በቀረበው እቅድ ላይ ከመከሩ በኋላ የገቢ ግብር፣ የታክስ አስተዳደርና የ2009 ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጆችን ተወያይተው እንደሚያፀድቁ ይጠበቃል።